የዝሆን ሎተሪ ወጣ
ዛሬ በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዕድል አዳራሽ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ ዝሆን ሎተሪ በህዝብ ፊት ወጥቷል፡፡
በዚህም መሰረት የወጡት የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች እንደሚከተሉት ሆነዋል ፦
1ኛ. 7,000,000 ብር የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ ቁጥር 0348349
2ኛ. 4,000,000 ብር የሚያስገኘው የ2ኛ ዕጣ ቁጥር 1523600
3ኛ. 2,000,000 ብር የሚያስገኘው የ3ኛ ዕጣ ቁጥር 1707653
4ኛ. 1,000,000 ብር የሚያስገኘው የ4ኛ ዕጣ ቁጥር 0042287
5ኛ. 500,000 ብር የሚያስገኘው የ5ኛ ዕጣ ቁጥር 0404416
6ኛ. 200,000 ብር የሚያስገኘው የ5ኛ ዕጣ ቁጥር 1669816
7ኛ. 100,000 ብር የሚያስገኘው የ5ኛ ዕጣ ቁጥር 1565394
8ኛ. 18 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 10,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 13294
9ኛ. 18 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 5,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 86624
10ኛ. 18 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 3,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 63652
* ተጨማሪ የዕጣ ቁጥሮችን ከላይ በተያያዘው ምስል ይመልከቱ !
ምንጭ፦ የብሄራዊ ሌተሪ አስተዳደር
“ጓደኞችዎን በጥበብ ይምረጡ”
ተማሪዎች አንድ ተማሪ ላይ ለመሳለቅ ፈልገው “እኔ ደደብ ነኝ” የሚል ወረቅት ጀርባው ላይ አጣብቀው ማንም እንዳይነግረው ተባባሉና እያዩት ይስቁበት ነበር ፡፡ መላው የክፍል ተማሪ በልጁ ግራ መጋባትና ጀርባው ላይ ባለው ፁሁፍ ምክንያት ከፍ ባለ ድምፅ ያስካኩ ነበር ፡፡ በዚህ መሃል የሂሳብ መምህር ክፍል ገባና ትምህርት ተጀመረ ፡፡ አስተማሪውም በቦርዱ ላይ አንድ ከባድ ጥያቄ ፃፈና መልሱን የሚያውቅ ፍቃደኛ ተማሪ ወጥቶ ይሰራው ዘንድ ጠየቀ ፡፡ ክፍሉ ውስጥ ከባድ ዝምታ ሰፈነ ፡፡ ወረቀት ጀርባው ላይ ከተለጠፈበት ተማሪ ውጪ እጁን ያነሳ አልነበረምና መምህሩ እድሉን ለሱ ሰጠው ፡፡ ተማሪው ወደፊት ሲወጣ ጀርባው ላይ ያለውን ወረቀት እያዩ ልጆቹ እንደጋና መሳቅ ጀመሩ ፡፡ መምህሩም በኃይል ተቆጥተው ገሰፇቸው ፡፡
ተማሪው አሁንም ግራ እንደገባው አስተማሪው ላቀረበው ውስብስብ የሂሳብ ጥያቄ ትክክለኛውን መልስ ከጥሩ ማብራሪያ ጋር አቀረበ ፡፡ ያን ሲያደርግ ሲስቁ የነበሩ ልጆች ሁሉ አፋቸውን ከፍተው ነበር በመደነቅ የሚያዩት የነበረው፡፡
አስተማሪው የልጁ ጀርባ ላይ ያለውን ወረቀት ቢመለከትም በተመስጦ ለጥያቄው መልስ ይሰጥ ስለነበር ሊያቋርጠው አልፈለገም ፡፡ በትክክል መልሱን እንደመለሰ ሲያይ በደስታ ስሜት ሄዶ አቀፈውና
ክፍሉን እንዲያጨበጭቡለት አደረገ ከዛም ጀርባው ላይ ያለውን ወረቀት አነሳና
“እዚህ ጎበዝ ተማሪ ላይ ይህን ወረቀት የለጠፈው ማነው?” አላችው በቁጣ ፡፡ከዚያም “ማን ይህን እንዳደረገ ቦሃላ ታወጣላቹ ከዛም ቅጣታቹን ታገኛላቹ ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ግን ሁለት ነገር ልንገራቹህ” በማለት ትኩረታቸውን ወደሱ እንዲያደርጉ አደረገ ፡፡
“በመጀመሪያ ፣ በሕይወታችሁን የወደፊት ግስጋሴ እና እድገታችሁን ለማስቆም ሰዎች ብዙ ይሞክራሉ ፡፡ ሃሜት ወሬ እና አሉባልታዎችን ያወሩባቸሁሃል ፡፡ በጣም ብዙ ስያሜዎችን ሊሰጧቹ ይችላሉ ። ለምሳሌ ይህ የክፍል ጓደኛችሁ ስለ ወረቀቱ ቢያውቅ ኖሮ ጥያቄውን ለመመለስ ባልተነሳ ነበር ፡፡
በህይወታቸሁ ውስጥ ማድረግ ያለባችሁ ነገር ቢኖር ሰዎች ለእናንተ የሚሰጧችሁን ስያሜዎች ችላ በማለት እና እራሳችሁን ለመማር ፣ ለማሳደግ እና ለማሻሻል እያንዳንዱን አጋጣሚ በመጠቀም ነው ፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ፣ ለዚህ ልጅ ስለ ተለጠፈበት ወረቀት የሚነግረው ከእናንተ መካከል ታማኝ ጓደኛ እንደሌለው ነው ፡፡
ምንም ያህል ጓደኞች ቢኖሩኑም ታማኝነት ከሌለው ዋጋ የለውም ፡፡ ከጀርባቹ ሊከላከልላቹ የሚችል ፣ ሊጠብቃቹ እና ከልቡ ስለእርስዎ የሚያስብልዎ ጓደኛ ከሌላቹ ብቸኝነት የተሻሉ ነው ፡፡ ከአስመሳይ ጋር ከመሆን ብቸኝነት በምን ጠአሙ”
_____________
ጓደኞችዎን በጥበብ ይምረጡ!
_____________
👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍
ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ፔጃችንን ላይክ እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ ያግዙን፡፡
https://www.facebook.com/branabooks/
👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍👍