ኢትዮጵያውያን እናቶች ከሚጠቀሙባቸው ባህላዊ መድኃኒቶች ጥቂቶቹን (ሼር ይደረግ!)
**********************************
ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹን በየቤታችን እናቶችን
ይጠቀሙበታል።
✅ #ጤና_አዳም
ቅጠሉም ሆነ ፍሬው ለሆድ መታወክ፣ ለቁርጥማትና ለሌሎች መሰል ሕመሞች መድኃኒት ነው።
✅ #ዳማከሴ
ለጉንፋን ፣ ለከባድ ራስ ምታት (ማይግሬን) በአፍንጫ ተስቦ የሚወሰድ ፣ ለመተንፈሻ ቧንቧ ችግርና አጠቃላይ ለምች ፍቱን መድኃኒት ነው።
✅ #ፌጦ
ለድንገተኛ ህመምና ውጋት ተወቅጦና ተበጥብጦ በመጠጣት ከህመም መፈወስ ይቻላል።
✅ #ጣዝማ_ማር
ከመሬት ተቆፍሮ የሚገኝ የማር ዓይነት ሲሆን ከነጭ አዝሙድና ኮረሪማ ጋር በመቀላቀል ጠዋት ጠዋት ሁለት ማንኪያ በመውሰድ ከሳል ፣ ከአስም ፣ ከቁርጥማት ወዘተ ህመም መገላገል ይቻላል። ይህንን መድኃኒት የወሰደ አንድ ሰው መድኃኒቱ እንዲሠራ ቢያነስ ከአንድ ሰዓት እስከ አንድ ሰዓት ተኩል ጊዜ ድረስ ሌላ ተጨማሪ ነገር እንዳይጠጣ ይመክራል።
✅ #ቀበርቾ
ከስራስር ክፍል የሚመደብ ሲሆን አገልግሎቱም ለድንገተኛ ህመም፣ ውጋት ወዘተ በማኘክ የሚወሰድ ፈዋሽ መድኃኒት ነው።
✅ #የነጭ_ባህርዛፍ_ቅጠሉ
ቅጠሉን በውሃ ተፈልቶ ቢታጠኑት የመተንፈሻ አካል ችግርም ሆነ የትኛውም የጉንፋን ዓይነትን ያለ ኪኒን በሁለት ቀን ውስጥ ፈውስ ያገኛል።
✅ #ነጭ_ሽንኩርት
ለደም ዝውውር ፣ ለጨጓራ ፣ ለውስጥ ካንሰር፣ ለመተንፈሻ አካል፣ ለወሲብ ማነቃቂያነት እና በሰውነት ውስጥ ምግብ እንዲንሸራሸር ፍቱን መድኃኒት እንደሆነ አዋቂዎች አብነት በመጥቀስ ይናገራሉ።
✅ #ቀይ_ሽንኩርት
ለአጠቃላይ ጤንነትና ለደም ዝውውር ጠቃሚ ከመሆኑም ባሻገር የዘር ፈሳሽ እጥረት ላጋጠማቸው ሰዎች በብዛት ለማመንጨት እንደሚያገለግል አባቶች ይናገራሉ ፤ ኮረሪማና ቆንዶ በርበሬ እነዚህ በአንድ ላይ ተቀምመው ለራስ ምታትና ለሆድ ቁርጠት ፍቱን መድኃኒት ናቸው።
✅ #ሬት
ቅርፊቱ ተልጦ የሚገኘው የውስጡ ዝልግልግ የማር ወለላ የመሰለው ነገር ከሌላ ምግብ ጋር አዋህዶ በመምታት የከሱ ሕፃናት ቢመግቡት ወዲያውኑ ያፋፋቸዋል፣ ለቁስል ቢቀቡት ወዲያው የመፈወስ ኃይል አለው ፣ ለፎረፎር ቢቀቡት፣ የስኳር በሽተኞችና የደም ግፊት ችግር ያለባቸው ሰዎች አድርቀው ፈጭተው እንደ ሻይ አፍልተው ቢጠጡት የመፈወስ አቅም አለው።
✅ #ግራዋ
ቀን ተመርጦ 7 ቅጠሉ ተቀንጥሶ በሰው እጅ መድኃኒት ለበላ ሰው ቢያጠጡት የመፈወስ ኃይል አለው ፣ እንዲሁም በግራዋ የታጠበ እቃ(እንስራ) ሽታን የሚያመጡ ባክቴሪያዎችን ያጠፋል። ከዚህ በተጨማሪም ግራዋ የተተከለበት ቦታ እባብ ፈፅሞ አይኖርም።
✅ #እንስላል
በውሃ ተቀቅሎ ሲጠጣ የተዘጋ የሽንት ትቦ ይከፍታል።
✅ #የምድር_እምቧይ
ስሩ ተወቅጦ የታመሙ ከብቶች እንዲጠጡት ሲደረግ ከብቶቹ ይድናሉ።
✅ #መቅመቆ
ስሩ ተወቅጦ እንዲደርቅ በማድረግ ዱቄቱ 2 ወይም 3 በሻይ ማንኪያ በውሃ በማፍላት እንዳሻይ ቢጠጣ የደም ግፊት ይቀንሳል።
✅ #የእንጆሪ_ቅጠል
በንፅህና ደርቆ ተወቅጦ በሻይ መልክ ተፈልቶ ቢጠጣ የስኳር ህመምን ይቀንሳል።
✅ #ሎሚ
ለብዙ ዘመናት ከምግብ መመረዝና ተያያዥነት ካላቸው ሌሎች ምክንያቶች የሚከሰት የሆድ በሽታ ለመፈወስ ሲጠቀሙት የቆየ ባህላዊ መድኃኒት ነው።
✅ #እንቆቆና_መስመስ
ለሆድ ትላትልና መሰል በሽታዎች ተፈጭቶና ተበጥብጦ ከኮሶ ጋር በመደባለቅና በመጠጣት ለኮሶ ትልና መሰል የሆድ ህመም መድኃኒት ነው።
✅ #የጥቁር_ገብስ_አረቄ
የጥቁር ገብስ አረቄ ለአስም በሽታ ጠዋት ጠዋት ሁለት መለኪያ ቢወስዱት በሽታውን ማስታገስ ይቻላል።
✅ #ሰንሰል_እና_አግራ
ሰንሰል ከሀገር በቀል መድኃኒት ውስጥ የሚካተት ሲሆን ቅጠሉን በመበጠስ ተወቅጦ በሻይ ብርጭቆ አንድ በባዶ ሆድ ሲጠጡበት በወፍ በሽታ ለተጠቃ ሰው ፍቱን መድኃኒት ነው።
✅ #ኮሶ
የደረቀ የኮሶ ዛፍ አበባ ከእንቆቆና መስምስ ወቅጦ በብርጭቆ በመጠጣት የሆድ ውስጥ ጥገኛ ትላትልን ጠራርጎ ማስወጣት ይቻላል።
✅ #ሽፈራው
የዚህ ዛፍ ቅጠል የማያድነው በሽታ የለም ይባላል የስኳር መጠንን ይቀንሳል ፣ የደም ግፊትን ይቀንሳል፣ የደም ዝውውርን ያቀላጥፋል ቅጠሉን.... እንደ ሻይ ተፈልቶ ፣ ዱቄቱ ተወቅቶ በውሃ መጠጣትም ይቻላል፤ እንዲሁም እንደ ጎመን ቀቅሎ መብላትም ይቻላል።
✴ እነዚህ እፅዋቶች እንደየ አከባቢው አጠራር ስማቸው ሊለያይ እንደሚችል ግንዛቤ ይወሰድ። ሼር ሼር
ምንጭ፦ኢትዮጵያን ፕረስ
ሼርርርር
