የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ የኮሮና ወረርሽኝን አስመልክቶ ኃያላን አገራትን ወቀሱ

Comments · 214 Views

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ የኮሮና ወረርሽኝን አስመልክቶ ኃያላን አገራትን ወቀሱ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ የኮሮና ወረርሽኝን አስመልክቶ ኃያላን አገራትን ወቀሱ


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የዓለም ታላላቅ አገራት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመዋጋት ተባብረው አልሰሩም ሲሉ ወቅሰዋል።

ዋና ጸሃፊው በቢቢሲ ሬዲዮ 4 ላይ ቀርበው እንደተናገሩት በአሁኑ ጊዜ በአሜሪካ፣ በቻይናና በሩሲያ መካከል ያለው ግንኙነት አጋጥሞ በማያውቅ ሁኔታ ተዳክሟል ብለዋል።

"የአሁኗ ዓለም በሁለት ወይም በበርካታ ኃያላን የምትመራ ልትሆን አትችልም። በብዙ መልኩ ትርምሶች ይታያሉ።

መግባባት አለመኖርና በኃያላን መካከል ያለው ፉክክር ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ብቻ ሳይሆን ለዓለም ዋነኛ ፈተና ነው” ብለዋል።

ጉቴሬዝ ጨምረውም የመንግሥታቱ ድርጅት የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት በሊቢያ፣ በየመን፣ በሶሪያና በአፍጋኒስታን ላሉትና በዓለም ዙሪያ ለሚካሄዱ ግጭቶች መፍትሄ እንዲፈልግ ጥሪ አቅርበዋል።

ዋና ጸሃፊው በዚህ ወረርሽኝ እየተስፋፋ ባለበት ጊዜ ባለጸጋ አገራት ድሃ አገራትን ለመርዳት አስፈላጊውን ነገር አላደረጉም ሲሉ ተችተዋል።

የዓለም መንግሥታት የኮሮናቫይረስ ክትባት የሁሉም አቅም ያገናዘበና ተደራሽ እንዲሆን መደገፍ እንዳለባቸው ጠቅሰው “ሁሉም ሰው ከወረርሽኙ የተጠበቀ ካልሆነ፤ ሁላችንም የተጠበቅን አንሆንም” ሲሉ ተናግረዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።
#ebc

Comments