ማላዊ የቀድሞ መሪ በማላዊ ኮሮናቫይረስ የለም አሉ

Comments · 142.4K Views

ማላዊ የቀድሞ መሪ በማላዊ ኮሮናቫይረስ የለም አሉ

ማላዊ የቀድሞ መሪ በማላዊ ኮሮናቫይረስ የለም አሉ 
የማላዊ የቀድሞ ፕሬዝደንት ጆይስ ባንዳ በምርጫ ቅስቀሳ ለተሰበሰበ ሕዝብ "ኮሮናቫይረስ በማላዊ የለም' ካሉ በኋላ የአገሪቱ መንግሥት በበሽታው ተያዙ እያለ የሚያወጣውን ሐሰተኛ አሃዝ ማቆም አለበት ብለዋል። 

የማላዊ ፖለቲከኞች ከ10 ቀናት በኋላ በአገሪቱ ዳግም በሚካሄደው ምርጫ ላይ ድምጽ ለማግኘት የምርጫ ቅስቀሳ እያካሄዱ ይገኛሉ። 

በማላዊ ከአንድ ዓመት በፊት ተካሂዶ የነበረውን የምርጫ ውጤት የአገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውድቅ ካደረገ በኋላ ማላዊ ሌላ ምርጫ ለማከናወን የመጨረሻ ዝግጅት ላይ ትገኛለች። 

ፖለቲከኞች የኮሮናቫይረስን ችላ በማለት በርካታ ደጋፊዎቻቸውን ለምርጫ ቅስቀሳ አደባባይ ሲጠሩ ቆይተዋል። 

በምርጫ የማይሳተፉት የቀድሞ ፕሬዝደንት ደጋፊዎቻቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አባል እጩዉን ላዛረስ ቻከዌራን እንዲመርጡ ጠይቀዋል። 

የቀድሞ ፕሬዝደንት ጆይስ ባንዳ ለደጋፊዎቻቸው ባደረጉት ንግግር ላይ የአገሪቱ መንግሥት የቫይረሱን ስርጭት እከላከላለሁ ብሎ የመደበውን በጀት ወደ ሌሎች የልማት ፕሮጄክቶች ላይ ፈሰስ እንዲያደርግ ጠይቀዋል። 

የማላዊ መንግሥት እስካሁን በአገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ 455 ሰዎች መገኘታቸውን እና 4 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ህመም ህይወታቸው ማለፉን ይፋ አድርጓል። 
#bbc

Comments