ኬንያ የለይቶ ማቆያ ማከሚያዎች በመሙላታቸው ህክምናው በቤት እንዲሰጥ ወሰነች

Comments · 779 Views

ኬንያ የለይቶ ማቆያ ማከሚያዎች በመሙላታቸው ህክምናው በቤት እንዲሰጥ ወሰነች

ኬንያ የለይቶ ማቆያ ማከሚያዎች በመሙላታቸው ህክምናው በቤት እንዲሰጥ ወሰነች

በኬንያ የኮሮናቫይረስ ህክምና የሚሰጥባቸው የለይቶ ማቆያ ማከሚያ ማዕከላት መሙላታቸውን ተከትሎ ለህሙማኑ ህክምና በቤት እንዲሰጥ መወሰኑን የሃገሪቱ ጤና ሚኒስትር አስታውቀዋል።

ሚኒስትሩ ሙታይ ካግዌ እንደተናገሩት፣ በመጀመሪያ ደረጃ በቤት ውስጥ ለሚደረገው ህክምና የሚያገለግል መመሪያ እንደሚወጣ እና በመቀጠልም የጤና ማዕከላቱን ነፃ ለማድረግም ህሙማኑ ወደየቤታቸው የመላክ ስራ ይሰራል ብለዋል።

በቤታቸው ሆነው ከኮሮናቫይረስ የሚያገግሙ ህሙማንም ላይ መገለል እና አድልዎ እንዳይኖር ሚኒስትሩ ተማፅነዋል።

በኬንያዋ መዲና ናይሮቢ ሁለት ለይቶ የማቆያ ህክምና መስጫ ማዕከል የሚገኙ ሲሆን በአሁኑ ሰዓትም መሙላታቸው ተገልጿል።

ሃገሪቷ በትናንትናው ዕለት 124 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን መመዝገቧን ተከትሎ፤ አጠቃላይ ቁጥሩንም 2 ሺህ 340 አድርሶታል። ከነዚህም መካከል 592 ሲያገግሙ 78ቱ ህይወታቸውን አጥተዋል።

በቤታቸው ሆነው ከኮሮናቫይረስ የሚያገግሙ ህሙማን ከሰዎች ጋር መቀላቀልን ማስወገድ፣ የራሳቸው የመኝታ ክፍልም እንዲኖራቸውም የአለም አቀፍ ጤና ድርጅት መመሪያ ያዛል።

ከህሙማኑ ጋር በጋራ እቃዎችን አለመጠቀም ወይም ፀረ- ተህዋሲያን (ዲስ ኢንፌክታንት) መርጨት እንዲሁም እንክብካቤ የሚሰጡ ግለሰቦችም መከላከያ ሊያደርጉ እንደሚገባም መመሪያው ያትታል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

Comments