ጆርጅ ፍሎይድ ኮሮናቫይረስ ነበረበት ተባለ

Comments · 736 Views

ጆርጅ ፍሎይድ ኮሮናቫይረስ ነበረበት ተባለ

ጆርጅ ፍሎይድ ኮሮናቫይረስ ነበረበት ተባለ

በፖሊስ መገደሉ በመላው አሜሪካ ተቃውሞ የቀሰቀሰው ጥቁር አሜሪካዊው ጆርጅ ፍሎይድ ከመሞቱ ከሳምንታት በፊት ኮሮናቫይረስ ተገኝቶበት ነበር ተባለ።

20 ገፅ የሚሆነውና ስለ አሟሟቱ የሚገልጸው ሪፖርት እንደሚያሳየው፤ ጆርጅ ሚያዝያ 3 ኮሮናቫይረስ ይዞት እንደነበር ያሳያል።

ነገር ግን የቫይረሱ ዘረ መል በአንድ ሰው ሰውነት ውስጥ ለሳምንታት ሊቆይ ስለሚችል፤ ጆርጅም የበሽታው ምልክት ሳይታይበት ሊቀር እንደቻለ ተገልጿል። ሪፖርቱ ጆርጅ “ቀደም ሲል ይዞት የነበረ በሽታ ያሳደረው ጉዳት” ይታያል ይላል።

የጆርጅ ፍሎይድን አስክሬን በግል ከመረመሩት ሁለት ሀኪሞች አንዱ የሆኑት ዶ/ር ማይክል ባደን፤ ለኒው ዮርክ ታይምስ እንደተናገሩት፤ ጆርጅ በኮቪድ-19 መያዙ አልተነገራቸውም ነበር ።

“የአስክሬን ምርመራ ሲደረግ ሟቹ ኮሮናቫይረስ እንደነበረበት ከታወቀ፤ አስክሬኑን ለሚነኩ ሰዎች ባጠቃላይ ማሳወቅ ይገባል። [ቢታወቅ] ጥንቃቄ ይደረግ ነበር” ብለዋል ዶ/ር ማይክል።

Comments