Juuki shared a post  
1 year ago

🤔🤔🤔

1 year ago

#wwiii

" 3ኛው የዓለም ጦርነት በኑክሌር የታገዘ እና አውዳሚ ይሆናል " - ሰርጌ ላቭሮቭ

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ዛሬ እንደተናገሩት ሶስተኛው የዓለም ጦርነት የሚካሄድ ከሆነ የኑክሌር ጦር መሳሪያን ያካተተ እና አውዳሚ ይሆናል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ላቭሮቭ ሀገራቸው ሩሲያ ፥ ኪየቭ የኑክሌር ጦር መሳሪያ ከያዘች " እውነተኛ አደጋ " ይጠብቃታል ያሉ ሲሆን ፤ ሀገራቸው ዩክሬንን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንድታገኝ እንደማትፈቅድ ተናግረዋል።

ከአንድ ቀን በፊት ሚኒስትሩ ዩክሬን የኑክሌር መሳሪያ ለመታጠቅ እየሞከረች መሆኑን ተናግረው ይህ ትልቅ ስጋት በመሆኑ ሊቆም እንደሚገባው አጥብቀው አስጠንቅቀው ነበር። በተጨማሪ ምዕራባውያን ሀገራት በቀድሞ ሶቪየት ኅብረት አገሮች ውስጥ የጦር ሰፈር እንዳይገነቡ አስጠንቅቀው ፤ ሩሲያ ዩክሬን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ለማግኘት የምታደርገውን ሙከራ እንደምታስቆም ተናግረው ነበር።

በሌላ በኩል ፤ ሰርጌ ላቭሮቭ ከዩክሬን ጋር የሁለተኛው ዙር የሰላም ድርድር እንደሚቀጥልና ሀገራቸውም ለዚህ ዝግጁ መሆኗን ገልፀዋል፤ ነገር ግን ዩክሬን የአሜሪካንን ትዕዛዝ እየተቀበለች መሆኑን ተናግረዋል።

ሩስያ በዩክሬን ላይ እያካሄደች የምትገኘውን ወታደራዊ ኦፕሬሽን ግቡን ሳይመታ ወደኃላ እንደማትመለስ እየገለፀች ትገኛለች።

imageimage