ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሰጡት መግለጫ ራያ እና ሽረ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መያዛቸውን አረጋግጠዋል።
ዶክተር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ፥ "በውጊያ መገፋፋት እንዳለ ድሮም እናውቃለን፤ አሁንም ገጥሞናል። ትላንት ጠላት ወደ ራያ እና ሽረ ገብቷል። ትግሉ አሁንም ቀጣይ ነው። ገና ነው። ውጊያ ውስጥ ነን። መገፋፋት እንዳለ ይታያል። ከነሙሉ አቅማችን ሆነን ነው ኣሁንም እየገጠምን ያለነው።" ብለዋል።
ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የህዝብ መፈናቀል መከሰቱ በትለይም በትግራይ ህዝብ ላይ ከባድ ችግር መድረሱን አንስተዋል።
ከትግራይ ጋር እየተዋጉ 'ያሉ ኃይሎች' በድሮን ጭምር ጉዳት እያደረሱ ነው ብለዋል ፤ መንግስታቸውም ሁሉን አቀፍ ትግል ማድረጉን እንደሚቀጥል በመግለጫቸው ገልፀዋል።
በሌላ በኩል ፦
ከትናንት በስቲያ 'የአውሮፕላን ጥቃት' ያስተናገደችው መቐለ ትናንት እና ዛሬ መረጋጋት ይታይባታል። ሁሉም የግል እና የመንግሥት ባንኮች ተከፍተዋል።
የነዳጅ እጥረት በመኖሩ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ መቀነስ ጀምሯል። የስልክ እና የኢንተርኔት ግልጋሎቶች እንደተቋረጠ ነው።

image