አድሎ ፈፃሚዎቹ የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች

አማራ ክልል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ችግር ላይ በወደቁበት በዚህ ወቅት አንዳንዱ አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ ሲያልፍ አንዳንዶቹ ደግሞ ቃል ከመግባት የዘለለ መሬት የወረደ ስራ ሲሰሩ አይታይም።

5 ሚሊዮን ህዝብ ችግር ላይ ይገኛል፤ የዓለም አቀፍ ረጂ ተቋማት ሆኑ የውጭ ሚዲያዎች ይህን ጉዳይ አላስጨነቃቸውም ፤ ምክንያቱን ጊዜ ይፈታዋል።

የአማራ ክልል አደጋ መከላከል ምግብ ዋስታና እና ልዩ ድጋፍ የሚሹ ኮሚሽን ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ የተቋቋሙ ዓለም አቀፍ ተቋማት የተቋቋሙበት ዓለም አቀፋዋ ህግጋትን ወደጎን ትተው አድሎ ሲፈፅሙ መመልከቱ እንዳሳዘነው ገልጿል።

በተደጋጋሚ የዩኒሴፍ ፣ የWFP ፣ የUNOCHA ዳንትሪ ዳይሬክተሮች ወደ አማራ ክልል ሄደው ውይይት አድርገዋል፤ ክልሉ ያለውን ችግር እና ስፋት በአግባቡ እንዲያዩት ተደርገዋል።

እስካሁን ግን አንድም ምላሽ አልተደረገም።

የክልሉ መንግስት መሰረታዊ የገለልተኝነት ችግር አለ ብሎ ያምናል።

ሰብዓዊነት ዘርን፣ ቀለምን፣ ሃይማኖትን፣ የፖለቲካ ልዩነትን የሚጠይቅ ጉዳይ አይደለም፤ ተቋማቱም ሲቋቋሙ ዘርን ሃይማኖትን ፣ ብሄርን፣ የፖለቲካ አመለካከትን ማዕከል አድርገው ድጋፍ ለማድረግ አይደለም የተቋቋሙት፤ ሰብዓዊነት ሁሉም ሰው በመሆኑ ብቻ የሚደረግ ድጋፍ ነው።

ተቋማቱ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ አይደለም።

የሰብዓዊ ድርጅቶቹ በዓለም አቀፍ ድንጋጌ መሰረት ችግር ላይ ያሉ 5 ሚሊዮን ዜጎችን የመታደግ ኃላፊነት አለባቸው።

የአማራ ክልል አሁንም ተቋማቱ ከተቋቋሙበት ዓላማ አንፃር ኃላፊነታቸውን በተገቢው መንገድ እንዲወጡና ህዝቡ ላይ እየደረሰ ያለውን ስቃይ እንዲታደጉ ጥሪ አቅርቧል።

image