" ... ከ5 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስገልገዋል " - የአማራ ክልል መንግስት
የአማራ ክልል አደጋ መከላከል ምግብ ዋስታና እና ልዩ ድጋፍ የሚሹ ኮሚሽን ፥ በክልሉ ህወሓት ወረራ በፈፀመባቸው ዞኖች ማለትም ፦
- ሰሜን ወሎ
- ደቡብ ወሎ
- ከፊል ደቡብ ጎንደር
- ዋግኽምራ ውስጥ የሚኖሩ እና ተፈናቅለው ያሉትን ጨምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ሲል አሳውቋል።

ህወሓት በከፈተው ጦርነት ከ991 ሺ በላይ ሰዎች የተፈናቀሉ ሲሆን በወረራ በተያዙ አካባቢዎች ደግሞ ከ5 ሚሊዮን ህዝብ በላይ አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል፤ እነዚህ ነዋሪዎች ለምግብ እጦት ፣ የመጠጥ ውሃ እና የመድሃኒት እጦት ችግር ተጋልጠዋል።

በሰሜን ወሎ ሜቄት አካባቢ ብቻ በህክምና እጦት 90 ሰዎች የሞቱ ሲሆን፤ በተመሳሳይ የወለሊድ አገልግሎት ባለመኖሩ ምክንያት 13 እናቶች ሞተዋል።

በጋዝጊብላና በዝቋላ አካባቢ በመድሃኒት እጥረት ፣ በምግብ እጦት 13 ሰዎች ሞተዋል።

በአጠቃላይ በወረራ ውስጥ ያሉ ነዋሪዎች ቤታቸውን እንደዘጉ በምግብ እና በመድሃኒት እጦት ሞተው የሚገኙበት ሁኔታ ነው እየተፈጠረ ያለው።

ከላይ የተገለፀው ቁጥር ሙሉ አይደለም ፤ ከዚህ በጣም ሊጨምር ይችላል፤ በየአካባቢው የመንግስት መዋቅር በመፍረሱ በምግብ እና በህክምና እጦት የሞቱ አጠቃላይ ሰዎችን ቁጥር ማወቅ አልተቻለም።

image