(.....)

ድምፅሽ ድምፄን ነካ
እዉነት በማስመሰል በዉሸት ተለካ
ሃቅሌን ሳትኩልሽ ሄሎ በሚል ቃና
ሳልረዳዉ ዉሉን ተዘጋ እንደገና
እንዴት ብየ ልመን
ምን ብየ ልክተበዉ
ተዘጋ?...ዘጋሽዉ?
መልሱ ግን ካ'ንች ነዉ

አወ ይገባኛል
በእኛ ዘመን ልኬት
የፍቅር መስፈሪያዉ እዉነት እንዳልሆነ
በዉሸታም ቀስቱ ሀቅን እንዳደነ

አንችዋ ምን ላድርግ
እቴዋ ምን ይብቃኝ
ዘመን አልቀለብስ
ወይ ሙቸ አልነሳ እዉነት እንዲገባኝ

እማስን ይዣለሁ
እኳትን ይዣለሁ
መልስ በማጣቴ መልስ እፈልጋለሁ

ጥያቄ?
ጥያቄ?
ለፍቅር ጥያቄ?
ለመኖር ጥያቄ?
ለመሞት ጥያቄ?

መጠየቅ በራሱ
ጥያቄ እያጫረ ከራስ ጋር ይፍጫል
ለመሞት መኖሬ
ለመሻር ህመሜ ለማን ይገባዋል?

ለማንም!!!

ሰካራሙ ገጣሚ(በረከት)
ወሎ-ወረኢሉ

image