መምጫ
።።።።።።።
ትመጫለሽ ብዬ
ትመጣለህ ብለሽ
በዘንባባ ሰርተሽ
ያኖርሽው ቀለበት
እኔ ሳልደርስበት
አንቺም ሳታስሪልኝ
በሁለት ጎጥ ሆነን
መንገድ ስጠብቂኝ
መምጫሽን ስናፍቅ
እንዳትቀሪ ሰጋሁ
ዘንባባው እንዳይደርቅ ፈራሁ
አንቺ ስጠብቂኝ
መጠበቄን ትቼ ወዳንቺ እዳልመጣ
ክሩ ሳይበጠስ ፀሀይዋ ሳትወጣ
ከመንገድ እዳትውይ ጠባቂሽ ሳይመጣ
ተነስቼ ነበር
ነገር ግን በሀገሩ
አንኳር በሌለበት በገለባው አለም
መጠበቂያ እንጂ መራመጂያ የለም።

image