Birtukan shared a post  
3 years ago

3 years ago

ሁሉም ነገር ለበጎ ነው!!

ሰውዬው የሚኖረው በአንድ አነስተኛ መንደር ሲሆን፣ ህይወቱን ለመምራት የሚፈይዱት ሶስት መሰረታዊ ነገሮች አሉት። ከወንዝ ውሀ የሚያመላልስለት አህያው የመጀመርያው ሲሆን፣ እንቁላሏን እየበላ እና እየሸጠ ህይወቱን የሚያቆይባት ዶሮ ሁለተኛዋ ናት። ሶስተኛው ደግሞ እነዚህን ሁለት እንስሳት እና ያሉትን እዚህ ግባ ማይባሉ ጥቂት ንብረቶች የሚጠብቅለት ውሻ ነው። ሰውዬ እኚህን መሰረታዊ ግልጋሎት የሚያቀርቡለትን እንስሳት እየተገለገለ ኑሮውን መምራት ከጀመረ ሰነባብቷል።

ከእለታት አንድ ቀን አህያው በለከፈው በሽታ ምክንያት ታሞ ይሞታል። ይህንን የተመለከትው ግለሰብ በጣም አዘን። ነገር ግን ከማማረር ይልቅ "ለኸይር (በጎ) ነው" ብሎ አሳለፈው። በበነጋታው ንብረቱን የሚጠብቅለት ውሻ የሞተውን አህያ ስጋ ስለበላ እሱም ይሞታል። ሰውዬው "ይሄ ነገር ምንድነው?! ቢሆንም ለኸይር (በጎ) ነው" በማለት ሁለተኛ መርዶውን በትዕግስት አሳለፈው። ቀናቶች አልቆዩም ሶስተኛዋ መሰረታዊ ግልጋሎት ሰጭ ዶሮ ሞተች። ይሄኔ ይህ ሰው "አላህ ያሰበው በጎ ነገርማ አለ። እንደዚህ ችግሮችን አያከታትልብኝም" ብሎ በፀጋ የደረሰበትን ችግር ተቀበለ። ለተወሰኑ ቀናት በድንኳኑ ውስጥ በችግር አሳለፈ።

ከምሽቶች በአንዱ እሱ የሚኖርበት መንደር ውስጥ ዘራፊዎች በለሊት ይገባሉ። የአካባቢውን ሰው ንብረት በአጠቃላይ ዘረፋ። ድንኳኖቻቸውንም አፈራርሰው፣ የሚገድሉትን ገድለው፣ ሴቶቻቸውን ደፍረው ወጡ። ሰውዬ ሀገር ሰላም ብሎ ጠዋት ከእንቅልፋ ሲነቃ አካባቢው ምድረ በዳ ሆኗል። ከመንደሩ የቀረው የሱ ድንኳን ብቻ ነበር። ነገሩ ምንድነው ብሎ ሲጠይቅ፤ ለካስ በአካባቢው አብዝሃኛው ሰው እንደሱ እንስሳ እያረባ ስለሚተዳደር ዘራፊዎቹ በየቤቱ ሲገቡ የነበረው ከሶስት በአንድ የእንስሳት ድምፅ ነበር። ወይ በአህያ ጩኀት፣ አልያም በውሻ፣ ወይም ደግሞ በዶሮ ድምፅ ነበር። በጊዜ እንስሳቶቹን በሞት የተነጠቀው ሰው ጌታው ለካስ ለበጎ ነገር ሲያሰናዳው እንደነበር ተረዳ። ምስጋናውም የላቀ ነበር።

ሁሌም በህይወታችን የሚገጥሙን መሰናክሎች ለእኛ በጎን እንጂ ክፋትን እንደማያመጡብን ልንገነዘብ ይገባል። ከደረሰብን መከራ በስተጀርባ በጎ ነገር እንዳለ ልናውቅና በፀጋ መቀበል የአመስጋኝ መገለጫ ነው።

ቻናላችንን ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። አስተያየት ካለዎትም አይንፈጉን። እናመሰግናለን!!

image