ቃል ኪዳን
ያኔ ቃልኪዳንህ ልቤን ያበረታው
ንገረኝ አንዳች ምንስ ሀይል ናደው
እስከ ነገ ድረስ አለሐኝ እያልኩኝ
በፍቅርክ ኮርቼ ለስንቱ አወራሁኝ
ዛሬ ግን አዘንኩኝ በደረሰኝ መልዕክት
ተኩዘሀል አሉ ትተሀው የኔን ቤት
እኔ እንኳን ታስሬ በአንተ ተፅናንቼ
ዛሬ እንዴት ይውጣልኝ አልቅሼ እንባዬ
አንተን በማስታወስ ስጦታ ስልክም
ሀዘን ሆነ መልስክ ለካ አለ ይሄም
እኔ መች አውቄ መሆንህን ስውር
ስትርቀኝ በድንገት እያለው በእስር
ግድ የለም ለጌታ ሁሉንም ትቻለው
አምላክ ይከፍለኛል እሱኮ ሀያል ነው