የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ባለ 12 ነጥብ ውሳኔዎች በማስተላለፍ ተጠናቀቀ።
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓ ጉባኤ ከግንቦት 17/ 2013 ዓ.ም እስከ ግንቦት 20 ቀን 2013 ዓ.ም ሲያካሒደው የሰነበተውን የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ 12 ነጥቦችን የያዙ ውሳኔዎችን በማስተላለፍ ዛሬ ማለዳ ተጠናቋል። ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ፓትርያርክ ተክለሃይማኖት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤን መግለጫ በንባብ አሰምተዋል።
መረጃው የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።



