#nebe
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤን ያሰናከሉ የህግ አስፈጻሚ አካላት ላይ ፍትሕ ሚኒስቴር ክስ እንዲመሰርት ጠየቀ።
ቦርዱ ይህን የጠየቀው ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ ጋር በተያያዘ ከሰሞኑ ያጋጠሙ መስተጓጎሎችን በተመለከተ ዛሬ መግለጫ በሰጠበት ወቅት ነው።
ቦርዱ የፓርቲዎችን ጠቅላላ ጉባኤ ያሰናከሉ የህግ አስፈጻሚ አካላት ላይ ፍትሕ ሚኒስቴር ክስ እንዲመሰርት ከመጠየቅ ባለፈ በመንግስት መስሪያ ቤቶች ስር የሚተዳደሩ ስብሰባ ቦታዎች እና አዳራሾች ለፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤ ክፍት እንዲሆኑም ውሳኔ አሳልፏል።
በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ መሰረት፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠቅላላ ጉባኤያቸውን ቢያንስ በሶስት ዓመት አንድ ጊዜ ማካሄድ አለባቸው።
የፖለቲካ ፓርቲዎች ይህን ግዴታቸውን ለመፈጸም በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ወቅት መስተጓጎል እየገጠማቸው እንደሚገኝ ምርጫ ቦርድ ገልጿል።
ባለፈው እሁድ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ እንዲሁም ከዛ ቀደም ብሎ የእናት ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ መስተጓጎሉ ይታወሳል።
#ኢትዮጵያ_ኢንሳይደር
#tikvahethiopia

