በአዲስ አበባ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 1,625 ደርሰዋል
በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ዛሬ ሰኔ 1/2012 ዓ/ም ድረስ በተደረጉ የላብራቶሪ ምርመራዎች 1,625 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።
ባለፉት 24 ሰዓት ቫይረሱ የተገኘባቸው 115 ሰዎች ሲሆኑ ከነዚህ መካከል 7 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ 17 ሰዎች በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው የተቀሩት 91 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክም ሆነ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌላቸው ናቸው።
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በአዲስ አበባ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው አንድ መቶ አስራ አምስት (115) ሰዎች ክፍለ ከተማ ፦
• አዲስ ከተማ - 18 ሰዎች
• ጉለሌ - 10 ሰዎች
• ቦሌ - 42 ሰዎች
• ልደታ - 5 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 13 ሰዎች
• የካ - 5 ሰዎች
• ቂርቆስ - 9 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 4 ሰዎች
• አራዳ - 5 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 2 ሰዎች
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 2 ሰዎች
አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ 1,625 ሰዎች ክፍለ ከተማ እንደሚከተለው ቀርቧል ፦
• አዲስ ከተማ - 428 ሰዎች
• ጉለሌ - 211 ሰዎች
• ቦሌ - 202 ሰዎች
• ልደታ - 201 ሰዎች
• ኮልፌ ቀራኒዮ - 154 ሰዎች
• የካ - 90 ሰዎች
• ቂርቆስ - 76 ሰዎች
• ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 72 ሰዎች
• አራዳ - 69 ሰዎች
• አቃቂ ቃሊት - 50 ሰዎች
* አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 72 ሰዎች
