ፎቶ ፦ ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ ኩራት !
በዓለም ሻምፒዮና ሀገራችን ኢትዮጵያ ከፍተኛ ድል እንድታመጣ ቡድኑን በመምራት ፣ በማስተባበር፣ አይዟችሁ በማለት፣ በማበርታት፣ አንድነቱን በማስጠበቅ ኮ/ር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ከፍተኛውን ሚና ተጫውታለች።
ከሰሞኑን በሚዲያ ላይ ቃሏን የሰጠችው የማራቶን የወርቅ አሸናፊዋ ጎተይቶም ገ/ስላሰ ደራርቱ ቱሉ " የኢትዮጵያውያን እናት " ስትል ነበር የገለፀቻት።
ደራርቱ አትሌቶቻችን ሲያለቅሱ አልቅሳ፣ ሲስቁ ስቃ ፣ ሲደሰቱ ተደስታ በአትሌቲክሱ ዘርፍ ሀገራችን እያስመዘገበች ላለው ከፍተኛ ድል ትልቁን ሚና እየተጫወተች ነው።
