በጾም ውስጥ ያለው ኃይል ከራሱ ከጌታ ኢየሱስ ነው። #ኃይለ_ኢየሱስን_እንጠቀም

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ ቆሮንቶስ የጾመው(ማቴ 4) ጾም ለራሱ አስፈልጎት አልነበረም። ግን ደግሞ በዚህ በጾሙ ውስጥ አዳም የወደቀባቸውን 3ቱን አርእስተ ኃጣውእ በማሸነፍ መከታችን ሊሆን ነበር። እነዚህም ሦስቱ አርእስተ ኃጣውእ 1. ሥሥት(አትብላ የተባለውን በመብላት)፣ 2. ትእቢት(አምላክ ሆናለው ብሎ በማሰብ)፣ 3. ፍቅረ ነዋይ(ያልተሰጠውን በመመኘት) ነበሩ። ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "እኔ ሕግና ነቢያትን ለመሻር አልመጣሁም ለመፈጸም እንጂ" የሚለውን የጌታን ቃል ሲተረጉም እንዲህ ይላል፡ "እኛን የሚያስገርመን.. ጌታ ሕግን መፈጸሙ ሳይሆን እኛ ራሳችን ደግሞ ሕግን እንድንፈጽም ስላደረገን(ስላስቻለን) ነው"

ጌታ በጾም ውስጥ ፈተናን ድል ሲያደርግ ለእኛም ጾምን የፈተና ድል መንሻ አድርጎ ነው የሰጠን። ስለዚህም ይህንን ጾም ጌታ አምላካችንን በመማጸን በጸሎትና በቅዱስ ቁርባን በማሳለፍ ፈተናዎችንን ሁሉ ከጌታ የተነሳ ድል በመንሳት ከክብር ወደ ክብር የምናድግበት ይሁንልን።

image