የአብይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት ቅድስት ይባላል። በዚህ ሳምንት ስለ እግዚአብሔር ቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆቿን ታስተምራለች። እግዚአብሔር ቅዱስ በመሆኑ የተቀደሰ ነገር ያስፈልገዋልና ሰው ሁሉ በቅድስና መንገድ በመመላለስ የክብሩ ባለቤት የመንግስቱ ወራሽ እንዲሆን እግዚአብሔር እኔ ቅዱስ ነኝ እና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ በማለት ስለማስተማሩ ሰፊ ትምህርት ይሰጥበታል።

ሰውም መላእክትም፣ ቦታም፣ ዕለትም ለእግዚአብሔር
በእግዚአብሔር ተቀድሰዋል። ቅዱሳን መላእክትና ቅዱሳን ሰዎች የእግዚአብሔርን ቅድስና ተረድተው እግዚአብሔርን በማመስገን ሲተጉ ቅዱሳት ቦታዎችና ዕለታት የቅዱሳኑ ነገር ሲታሰብባቸው፣ ፀሎት ሲደርስባቸው እና ለእግዚአብሔር እና እግዚአብሔር ለቀደሳቸው ቅዱሳን ስም መጠሪያ ሆነው ሲያገለግሉ ይኖራሉ።

እግዚአብሔርን ማየትና የእግዚአብሔር የሆነን ስርዓት መከተል ስለሚያስችል ዕለት ዕለት መልካም በማድረግ ቤተመቅደስ ተብሎ
የተነገረለትን ሰውነታችንን በመጠበቅ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ዕቃ ሆነን መቅረብ እንደሚገባ ይዘከርበታል።

እግዚአብሔር አምላካችን ቅዱስ ነው እያልን በልባችን አምነን በአፋችን መስክረን በተግባር ግን ከቅድስና ርቀን እንዳንኖር እግዚአብሔር እንደቀደሰን እና ልጅነት እንደሰጠን በማመን በተቀደሰ ሁኔታ መኖር ይገባናል። መልካም ጾም

image