የነዳጅ ዋጋ 📈

ከነገ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሬ መደረጉን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳውቋል።

በዚህ መሰረት ፦

⛽️ ቤንዚን ➡️ 47. 83 በሊትር
⛽️ ነጭ ናፍጣ ➡️ 49.02 በሊትር
⛽️ ኬሮሲን ➡️ 49.02 በሊትር
⛽️ ቀላል ጥቁር ናፍጣ ➡️ 53.10 በሊትር
⛽️ ከባድ ጥቁር ናፍጣ ➡️ 52.37 በሊትር
⛽️ የአውሮፕላን ነዳጅ ➡️ 98.83 በሊትር መሆኑን አስታውቋል፡፡

ከላይ የተገለጸው የቤንዚን ፣ የኬሮሲን እና የነጭ ዋጋ ላይ ለህዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች ወይም የታለመ ድጎማ ተጠቃሚ ተሸከርካሪዎች 15 በመቶ በመንግስት እንዲደጎሙና ቀሪውን 10 በመቶ እንዲከፍሉ በማድረግ የድጎማ መጠኑን በቴሌ ብር ተመላሽ እንዲሆንላቸው ይደረጋል ተብሏል።

የተደረገው የዋጋ ማስተካከያ የተደረገባቸው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በዝርዝር ከነገ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክልሎች በሚገኙ ማደያዎች ሁሉ ተግባራዊ ይሆናል።

ምንጭ፦ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

imageimage