ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 3,410 የላብራቶሪ ምርመራ አርባ ስድስት (46) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 701 ደርሷል፡፡
ቫይረሱ የተገኘባቸው 29 ወንድ እና 17 ሴት ሲሆን የዕድሜ ክልላቸው ከ12 እስከ 79 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 45 ሰዎች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ አንዷ የእስራኤል ዜጋ ናት።
ቫይረሱ የተገኘባቸው 13 ሰዎች ከአዲስ አበባ (4 ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው ፣ 1 ሰው የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያለው እና 8 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው) ፣ 3 ሰዎች ከትግራይ ክልል (ሁሉም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸውና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉ)፣ 15 ሰዎች ከአማራ ክልል (ሁሉም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸውና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉ)፣ 11 ሰዎች ከሶማሌ ክልል (ሁሉም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸውና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉ) እንዲሁም 4 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው የድንበር ተሻጋሪ መኪና አሽከርካሪዎች ናቸው።
የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦
• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 34
• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው - 4
• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌላቸው - 8
ተጨማሪ መረጃ ፦
በትላንትናው ዕለት 8 ሰዎች (2 ሰዎች ከደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል ፣ 6 ሰዎች ከአዲስ አበባ) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 167 ደርሰዋል።