በትግራይ ክልል ምርጫ ባይቶና አንድ ወንበር ማግኘቱ መገለፁ ይታወሳል ፣ ዛሬ ፓርቲው በሰጠው መግለጫ ወንበሩን ሊረከብበት የሚያስችል የሕገ አግባብ አለመኖሩ ገልጿል፡፡
ባይቶና በምርጫው ያገኘው 93,945 ድምፅ አንድ ወንበር ሊያስገኝለት የሚችል ሕጋዊ የቁጥር ስሌት አለመኖሩን ፣ ይልቁንስ የቀረው አንድ ወንበር ለህወሓት እንደሚገባ ፓርቲው ጠቁሟል፡፡
ከዚህ ውጭ ባይቶና በምርጫው ሂደት በርካታ ሕገ-ወጥ ተግባራት መፈፀማቸውን ጠቅሶ አውግዟል።
- በምርጫው ዕለት የባይቶና ታዛቢዎች በፖሊስ ከምርጫ ጣብያዎች እንዲወጡ ተደርጓል፣
- እጩዎች ታስረዋል፣ ዛቻ ደርሷቸዋል፣
- ህዝብ አማራጭ ፓርቲ እንዳይመርጥ በገዢው ፓርቲ ታችኛው መዋቅር ማስፈራራት ተፈፅሟል፣
- ለምረጡኝ ቅስቀሳ የተከራያቸው መኪና ባለቤቶች ታስረዋል የሚሉና ሌሎች ቅሬታዎች ከባይቶና ተነስተዋል፡፡
በዚህ ሁሉ ችግር መካከል ባይቶና ፓርቲ ቀላል የማይባል ድምፅ ማግኘቱ እና "የመጪው ግዜ ፓርቲ" መሆኑ አሳይቷ ሲሉ የፓርቲው ቃል አቀባይ አቶ ክንፈገብርኤል ገብረዮሐንስ መናገራቸውን የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።
