#የዛሬው_ታላቅ_መልዕክት
የያዝከው ነገር በቂ መስሎ ካልታየክ፤ድፍን አለምን ብትጨብጥ እንኳን፤ ሀዘንተኛ እንጂ ደስተኛ መሆን አችልም፤
እናም ባለህ ነገር ፈጣሪን አመስግነህ ኑር።
የሰው ዋጋው እየቀነሰ የዶሮ እና የእህል ዋጋ እየጨመረ ሲመጣ በርትተህ ፀልይ ፡፡
ሰዎች ስለ አንተ መጥፎነት ቢያወሩ አይድነቅህ ምክንያቱም ውሾች በማያውቁት ሰው ላይ ነው የሚጮሁት
ጨውን ሺ ጊዜ ስኳር ብትለው ስሙን እንጂ ጣአሙን መቀየር አችልም።
ከክፋት ስትርቅ ሰላምህን ታበዛለህ፤ቅንና መልካም ስትሆን ደሞ ከጭንቀትና ከጸጸት ትድናለህ። በሕየውትህ ሰዎችን ለመረዳት እንጂ ለመጉዳት አታስብ።
ፍቅርና መልካምነት ከቃል ይልቅ መተግበርን ይፈልጋል።
የውሸት ጎደኛ እና ጥላ ሁለቱም አንድ ናቸዉ ሁለቱም ፀሐይ እስካሉ ድረስ ነው።
🔶 ️ውሾች እና ድመቶች አልጋህ ላይ እንዲዘሉ እየፈቀድክ ድሆች ግን የግቢህ ድንጋይ ላይ እንዲቀመጡ ባለመፍቀድህ የፈጣሪህን ምህረት ጠይቅ፡፡
🔶️ ከዚህ አፍ እና ልብ ከተለያዩበት ቲያትረኛ ማንነትህ ፈጥነህ ውጣ።
🔶 ️የሳቀልኝ ሁሉ ሰው እየመሰለኝ ጠላቴን ስጠብቅ ወዳጄ ገደለኝ
🔶️ ሰዎች ሆይ የሚቀድመውን ብናስቀድም የማይተወን ፈጣሪ ይከተለን ነበር ፡፡
