#news
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የዴልሂ ግማሽ ማራቶንን በሁለቱም ፆታዎች ድል አደረጉ
-----------------------------------------
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በህንዷ ዋና ከተማ ዴልሂ በተካሄደው ኤርቴል ግማሽ ማራቶን በሁለቱም ፆታዎች ውድድሩን በበላይነት አጠናቀዋል።
በወንዶች ዘርፍ አትሌት አምደወርቅ ዋለልኝ 58:53 ጊዜ ሮጦ በአንደኝነት በማጠናቀቅ የቦታውን ሰአት በማሻሻል አሸንፏል።
አትሌት አምደወርቅ በቅርቡ ፖላንድ ተካሂዶ በነበረው የአለም ግማሽ ማራቶን 3ኛ በመውጣት የነሀሃስ ሜዳሊያ ተሸልሟል።
በውድድሩ ሌላኛው አትሌት አንዱ አምላክ በልሁ 2ኛ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በግማሽ ማራቶን የተሳተፈው አትሌት ሙክታር ኢድሪስ 4ኛ ደረጃ አግኝቷል።
እንዲሁም በሴቶች የአለም የግማሽ ማራቶን የነሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚዋ አትሌት ያለምዘርፍ የኃለው ግማሽ ማራቶኑን በ64:46 ጊዜ በመግባት የቦታውን ሰአት ጭምር በማሻሻል አሸንፋለች።
በውድድሩ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት አባብል የሻነው 3ኛ ስትወጣ ፤ጸሃይ ገመቹ 5ኛ ደረጃን አግኝታለች።
#news
በኢትዮጵያ 604 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ 1065 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል
————————————————————————
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 5 ሺህ 466 የላቦራቶሪ ምርመራ 604 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 109 ሺህ 534 ደርሷል።
በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 1065 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 69 ሺህ 315 ሆኗል።
ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 700 ደርሷል።
በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 38 ሺህ 517 ሰዎች መካከል 322 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።
በአገሪቱ እስከ ዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊየን 631 ሺህ 912 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።
#news
መከላከያ የጁንታውን ምሽግ መቀሌን መቆጣጠሩን ተከትሎ ህዝቡ ደስታውን እየገለጸ ነው
👉የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መከላከያ ሰራዊት በትናንትናው እለት የጁንታውን የመጨረሻ ምሽግ መቀሌን መቆጣጠሩን ተከትሎ ደስታቸውን እየገለፁ ነው።
👉ትላንት ምሽት የባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ደብረ ታቦር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ኮሶበር፣ ወረታ፣ አዲስ ዘመን፣ ዳንሻ፣ ወልድያ፣ ቆቦ እና የሌሎች ከተማ ነዋሪዎች የህወሓት ጁንታ በመሸነፉ ደስታቸውን ገልፀዋል፡፡
#news
የ2012 ዓ.ም ተመራቂ ለነበሩ ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ ጥሪ እንደሚደረግ ተገለጸ‼️
↘️ በ2012 ዓ.ም ተመራቂ የነበሩ ተማሪዎች ከነገ ኅዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ጥሪ እንደሚደረግ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
↘️ ሚኒስቴሩ ለኢቢሲ በላከው መግለጫ ከአንድ ሳምንት በኋላ ሌሎች ቀሪ ተማሪዎች እንዲገቡ እና በዚህ የትምህርት ዘመን የሚጠበቅባቸውን ሦስት የትምህርት ሴሜስቴር እንዲያጠናቅቁ በቂ ድጋፍ እና ክትትል ሊደረግላቸው ይገባል ሲል ገልጿል።
↘️ ተማራቂ ተማሪዎች በቀሪዎቹ አጭር ወራት ውስጥ ያልተጠናቀቁ የትምህርት እና ሥልጠና ተግባራትን በተቻለ ቅልጥፍና እና ዝግጁነት በማጠናቀቅ ተመርቀው ወደ ሥራ ዓለም እንዲትቀላቀሉ እና የኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ ላይ አሻራቸውን እንዲያኖሩ አሳስቧል።
Tesfahunegn Demeke
Delete Comment
Are you sure that you want to delete this comment ?