👆👆👆የጅማ ዩኒቨርሲቲ የዐይን ህክምና ትምህርት ክፍል በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ተገድቦ የነበረዉን የህክምና አገልግሎት በቴሌመዲሲን ለማስቀጠል ዝግጅቱን አጠናቋል
******************
እንደሚታወቀው የኮሮና ወረርሽኝ በዓለም አቀፍ ደረጃ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የዐይን ህክምና ትምህርት ከፍል ለህብረተሰቡ በሚሰጣቸው ዐይንን የማከምና የመጠበቅ ግልጋሎት ላይ እንቅፋት ሆኖ ቆይቷል፡፡ ይህ ትምህርት ክፍል በደቡብ ምህራብ ኢትዮጲያ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የዐይን ህክምና ግልጋሎቶችን በጊዜና ቦታ ሳይወሰን ህብረተሰቡ ድረስ በዘመቻ መልክ በማዳረስ የሚታወቅ የህክምና ትምህርት ክፍል ነው፡፡
በአሁኑ ወቀት የተከሰተው ወረርሽኝ የጤና ባለሙያዎችን በማያጋልጥ መልኩ አገልግሎቱን ማዳረስ አስቸጋሪ አድርጎት ቆይቶዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ከፍተኛና ተከታታይነት ያለው ህክምና በሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ ይገኛል፡፡ የትምህርት ክፍሉ ይህንን ተግዳሮት ለመቅረፍና ለታካሚዎች የሚሰጠውን አገልግሎት ቀጣይነት ለማረጋገጥ የተለያዩ ጥረቶች ሲያደርግ የቆየ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም የOptalmic-Tele ማማከሪያ ክልኒክ አቋቁሞ በይፋ አገልግሎቶ መስጠት ጀምሯል፡፡
ይህ Tele የማማከሪያ ክሊኒክ በዋነኛነት የተቋቋመው የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ወደ ህክምና ማዕከሉ በግንባር ቀርበው መታከም ለማይችሉ ታካሚዎች ነው፡፡ በዚህ ክሊኒክ አማካኝነትም ትምህርት ክፍሉ መረጃ የመስጠት፣ የማማከር አገልግሎት፣ የታዘዙ መድሀኒቶች ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ የመስጠት፣ ተጨማሪ ምርመራና ህክምና የማያስፈልጋቸው የጤና ችግሮች ላይ የማማከርና ከፍተኛና ለአደጋ የሚያጋልጡ ህመም ያለባቸውን ታካሚዎች በአስቸኳይ የሆስፒታል ህክምና እንዲያገኙ ሁኔታዎችን የማመቻቸት አገልግሎት ይሰጣል፡፡
እነዚህን አገልጎሎቶች በአፋጣኝ ለማግኘት የምትህርት ክፍሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የስልክ ቁጥሮች ዝግጁ ያደረገ ሲሆን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን የሚፈልጉ ታካሚዎች ከቤታቸው ሳይወጡ በስልክ ቁጥሮቹ በመደወል ከጤና ባለሙያዎቹ በቀጥታ የምክር አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- 0942691335/ 0938899327
የጅማ ዩኒቨርሲቲ የዐይን ህክምና ትምህርት ክፍል ለህብረተሰቡ ነፃ የህክምና አገልግሎቶች በተለያዩ ቦታዎች በመዘዋወር በመስጠት የሚታወቅ የህክምና ትምህርት ክፍል ነው፡፡ በነዚህ በተለያዩ የአገልግሎት መስጠት ዘመቻዎች ከመጋቢት 16-20, 2012 ዓ.ም ብቻ እስከ አስር ሺህ (10,000) ለሚደርሱ ህመምተኞች ከHimalyan Cataract Project እና Vision Care Ethiopia ጋር በመተባበር አገልግሎት ያበረከተ ሲሆን ይህም የተከናወነው ወረርሽኙ ከመከሰቱና ሀገሪቱ የእንቅስቃሴ ገደቦችን በህግ ከመደንገጓ ጥቂት ጊዜ ቀደም ብሎ ነው፡፡
እቤትዎ በመሆን ከኮሮና ቫይረስ እራስዎን ይጠብቁ! የዐይን ህክምና ባለሙያዎችን ያማክሩ!
ጅማ ዩኒቨርሲቲ