ExpressAfrica
    • Advanced Search
  • Join
    • Login
    • Signup
ቤተ መጻሕፍት Cover Image
User Image
Drag to reposition cover
ቤተ መጻሕፍት Profile Picture
ቤተ መጻሕፍት
  • My Wall
  • Groups
  • Following
  • Followers
  • Likes
  • Photos
  • Videos
ቤተ መጻሕፍት profile picture
ቤተ መጻሕፍት shared a post  
29 days ago

The Dad's Life profile picture
The Dad's Life
29 days ago

image
Like
Comment
ቤተ መጻሕፍት profile picture
ቤተ መጻሕፍት
4 months ago

የምክር ስንቅ ( seasonal advices)
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
1- ☞ለምታሳድጋቸው ዶሮዎች እህልና አሽዋ ቀላቅለህ ብትሰጣቸው ዶሮዎቹ የሚበሉት የትኛውን ይመስልሃል ? እህሉን እንደምትለኝ እርግጠና ነኝ ፡፡ አንተም በመንፈሳዊ ሕይወትህ የሚጠቅመውን ከማይጠቅመው መለየትን ልመድ ፡፡
የያዝከውን እምነት ፈትሸው ፣ የሌሎቹንም በበጎ ህሊና ማንበብ መረዳት ። የተሻለውን መምረጥ ። ምክንያቱም በመልካም ማሳ ውስጥ ማይጠቅም እንክርዳድ ወይም አረም አይጠፋምና ፡፡
2-☞አምስት ዶሮዎች አሉህ ብለን እንገምት ለአምስቱ ዶሮዎችህ ሀያ አምስት ጥሬ ብትበትንላቸው ለእያንዳንዱ ዶሮ ስንት ስንት ጥሬ ሚደርሳቸው ይመስልሃል ? .. 25÷5=5 የሚል ከሆነ መልስህ በእርግጥም መሳሳትህን አስብ ፡፡

ምክንያቱም በዶሮዎቹ የሚደርሳቸው ጥሬ የሚወሰነው በዶሮዎቹ ቅልጥፍናና የመፍዘዝ ደረጃ የሚወሰን ነው ፡፡
አንተም በ ሕይወትህ በጎ በጎውን ነገር በቅልጥፍና መያዝን ልመድ ፡፡
3-☞የቤትህ በራፍ ሰባት ክንድ ከፍታ ቢኖርውም ዝቅ ብሎ መግባትን ልመድ ምክንያቱም ለቤትህ ያለህ ፍቅር የሚለካው ራስህን ዝቅ አድርገህ በመግባትህ ነው ፡፡
4-☞ወደ ላይ ለመውጣት ከፈለክ ወደ ታች መውረድን በሕይወት ዘመንህ ተለማመድ ምክንያቱም ወደ ታች ይበልጥ በወረድህ ቁጥር ለከፍታህ የሚረዳህን ሥር ለመያዝ አትቸገርም ፡፡ ሥር የሌለው ዛፍ ራሱን ችሎ መቆም አይችልምና ፡፡
5-☞ሰዎች ሲገፉህ ተገፋሁ ብለህ አትማረር ፡፡ ምክንያቱም ወተት ባይገፉ ኖሮ ቅቤ ሆኖ የመውጣቱ ነገር አጣራጣሪ ነበር ፡፡ ቅቤ መሆኑ ግን አናት ላይ ወጥቶ መቀመጥ ነው ፡፡ ስትገፉ ነገር ሁሉ ለበጎ ነው ማለትን ልመድ ፡፡
6-☞ማነህ ተብለህ ስትጠየቅ እኔ ነኝ ብለህ ለመናገር በማትደፈርበት ቦታ በፍፁም አትገኝ ፡፡ የሄድክበትን መንገድ ልብ ብለህ ማየትን ልመድ ፡፡ ምክንያቱም ስትመለስ ሊጠፉህ ስለሚችል ፡፡
7-☞በህይወት ዘመንህ ልትማርባቸው የሚገቡ ሶስት ነገሮች ብቻ አሉ ፡፡ አይተህ ሰምተህ ተሳስተህ ፡፡ ከእነዚህ ከሦስቱ በአንዱ መማር ካልቻልክ ግዑዝ አካል መሆንህን ከአሁኑ እወቅ ፡፡ አይቶ ሰምቶና ተሳስቶ መማር የማይችል ግዑዝ አካል ነውና ፡፡

image
Like
Comment
Share
ቤተ መጻሕፍት profile picture
ቤተ መጻሕፍት
5 months ago

ለአዕምሮ ጤና 10 ነጥቦች


❇ አእምሮ ማዘዣ ጣቢያ ነው በቫይረስ መጠቃት የለበትም፡፡ ሁልጊዜ ሊጸዳ ይገባዋል አእምሮ ከተወዛገበ ሌሎች የሰውነት አካላት መግባባት ያቅታቸዋል፡፡ አእምሮዎ በአስቀያሚ ቫይረሶች እንዳይጠቃ ማታ ማታ “ስካን” ያድርጉት፡፡ እንዴት ካሉ- በቀን ውስጥ ለ30 ደቂቃ ለብቻዎ ሆነው ወደ ውስጥ ያሰላስሉ፡፡ በቀን ውስጥ ጥሞና (meditation) ለ30 ደቂቃ ያስፈልጎዋታል፡፡ ደስ የሚሉዎትን ነገር እያሰቡ አእምሮዎን ዘና ያድርጉት፡፡

❇ አእምሮ ዕለታዊ ተግባራትን እንዳያከናውን ከሚፈትኑት ነገሮች አንዱ መጠጥ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ አደገኛ ዕጽ ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ጫት ነው፡፡ እነዚህ በሙሉ ይነስም ይብዛ አእምሮን ይመርዛሉ፡፡ ማናቸውም አእምሮን ጤናማ ባልሆነ መልኩ የሚያነቃቁ ዕጾች ተግባሩን ያውኩታል፡፡ ያስወግዷቸው፡፡

❇ አእምሮ በቀን ውስጥ ምን መስራት እንዳለበት ካልተነገረው ድብርት ውስጥ ይገባል፡፡ በቀን ውስጥ ምን መከወን እንዳለብዎ፣ ምን ምን ማሳካት እንደሚፈልጉ ይንገሩት፡፡ ያንን እንዳሳካ ሲገባው አእምሮ ዘና ይላል፡፡

❇ አእምሮዎ ልክ እንደ ጡንቻ ነው፡፡ ብዙ ሥራ ባሰሩት ቁጥር እየጠነከረ ይመጣል፡፡ አዳዲስ ነገሮችን መማር ይፈልጋል፣ አዳዲስ ተግዳሮቶች፣ አዳዲስ ፈተናዎች፣ አዳዲስ ጥበቦች እንዲማር እድል ይስጡት፡፡ በዚህ ዘመን 5+9 =14 የሚል ሂሳብ ለመስራት እንኳን ካልኩሌተር ነው የምንጠቀመው፡፡ የቅርብ ጓደኛችንን ስልክ በቃላችን ለመያዝ እንሰንፋለን፡፡ አእምሮ ከሰነፈ ይለግማል፡፡ አእምሯችሁን ቦዘኔ አታድርጉት፡፡ እንዳይዝግባችሁ መጽሐፍ አንብቡለት፡፡

❇ ጥሩ ምግቦች አእምሮ ስል እንዲሆን ያደርጉታል፡፡ የአሳ ዘይትና ሌሎች የተመጣጠኑ ምግቦችን በቀን በቀን ካገኘ ሥራ ማቀላጠፍ ያውቅበታል፡፡ በቂ ውኃ መጠጣት ለአእምሮ እንደ ግሪስ ያገለግላል፡፡

✴ አእምሮ በቫይረስ ይጠቃል፡፡ የአእምሮ ቫይረስ ምን እንደሆነ ያውቃሉ? አሉታዊ አስተሳሰቦች፡፡ ምቀኝነት፣ ክፋት ማሰብ፣ በማይረቡ ነገሮች መጨነቅ አእምሮን ያውካሉ፡፡ ይህን ቫይረስ ለማጽዳት መልካም መልካሙን ማሰብ ብቻ ይበቃል፡፡

✴ ቁርስ አይዝለሉ፡፡ መኪናዎ ማለዳ ተነስተው እንደሚያሞቋት ሁሉ አእምሮዎንም በአሪፍ ቁርስ ያነቃቁት፡፡ ቀኑን ሙሉ በንቃት እንዲሰራ ጥሩ ቁርስ ያስፈልገዋል፡፡

✴ ተሸፋፍነው አይተኙ፡፡ አእምሮ እጅግ ብዙ መጠን ያለው ኦክሲጂን የሚፈልግ የሰውነት ክፍል ነው፡፡ ሲታፈን ግራ ይገባዋል፡፡ መኪና የሚበዛባቸው ስፍራዎች፣ ኢንደስተሪዎች፣ ብዙ ሲጋራ የሚጨስባቸው አካባቢዎችን ያስወግዱ፡፡ በተቃራኒው መናፈሻ፣ አረንጓዴ ተክሎች የሚበዙባቸው ሜዳማ ስፍራዎች የእግር ጉዞ ቢያደርጉ አእምሮ በጣም ያመሰግንዎታል፡፡

✴ የከሰል ጭስ ለአእምሮ መርዝ ነው ብዙ ሰዎች ይህን ባለመረዳት ቤታቸውን በእጣንና በከሰል ጭስ ያፍናሉ፡፡ በነጋታው ኃይለኛ ራስ ምታት ያማቸዋል፡፡ የከሰል ጭስ አእምሮን ሊገድለው ይችላልና ይጠንቀቁ፡፡

✴ ለእርስዎ የማያስደስትዎትን ነገር ለሰው ሲሉ ብቻ አያድርጉ፡፡ የማያምኑበትን ነገር በፍጹም አይተግብሩ፡፡ ወደፊት ለጸጸት የሚዳርግዎትን መልካም ያልሆነ ተግባር በድብቅም ቢሆን አይስሩ፡፡ ፀፀትና የሕሊና ወቀሳ ለአእምሮ መርዛማ ነገሮች ናቸው፡፡ ሙሰና፣ ከትዳርዎ ውጭ መማገጥ፣ በሰው ላይ ተንኮልና ሴራ መፈፀም አእምሮን እስር ቤት ውስጥ ማጎር ማለት ነው፡፡ አእምሮ ሰላሙን አጥቶ ሰላምዎን እንዳይነሳዎ መልካም መልካሙን ብቻ ያድርጉ፡፡

image
Like
Comment
Share
ቤተ መጻሕፍት profile picture
ቤተ መጻሕፍት
5 months ago

ይህን ያውቁ ኖሯል

✅ አንድ ጤናማ ጉርሻን ለመዋጥ ከ 8 እስከ 12 ሴኮንዶች
ይፈጃል። ይህም ከአፍ እስከ ጨጓራ እስኪደርስ የሚወስደው ጊዜ ማለት ነው።

✅ የሴት ልጅ ልብ ከወንድ ልብ በበለጠ በፍጥነት እንደሚመታ ያውቃሉ።

✅ ወንድ ልጅ በአንድ ግብረ ስጋ ግንኝነት ጊዜ 30 ደቂቃ
ሊያስሮጠው የሚችል ካሎሪ ያወጣል።

✅ ማስቲካ ማኘክ ክብደት ይቀንሳል። ምክንያቱም ሰውነቱ ውስጥ ያለው የሜታቦሊክ ሂደት በ20 ፐርሰንት ስለሚጨምር ነው።

✅ ግመል በደቂቃ ውስጥ ብቻ 21 ጋሎን ውሀ በአንድ ትንፋሽ ይጠጣል።

✅ ኪዊ የተባለችው ወፍ የምትጥለው እንቁላል ከሰውነቷ ይዘት ይበልጣል።

✅ በጨረቃ ላይ ጠፈርተኞች የተጫወቱት ስፖርት ቢኖር 'ጎልፍ' ነው።

✅ ማርያ ባውሳራ ላራ የተባሉ የ67 ዓመት ስፔናዊት አዛውንት በ2006 ዓ.ም መንታ ልጆችን በኦፕራሲዮን ተገላግላለች።

✅ 23 ጊዜ አግብታ የፈታችው አሜሪካዊት የጊነስ ክብረ ወሠን ባለቤት ''ሊንዳ ዎልፍ'' ባሎቿን በቅድመ ተከተል እንደማታስታውሳቸው ትናገራለች። የመጀመሪያውን ባሏን ''ጆርጅ ስኮት'' ን ግን ሁሌም እንደምታስታውሠው ትናገራለች። እሱን ያገባችው የ16 ዓመት ኮረዳ እያለች ነው።

✅ 26,000 መስኮቶች ያሉት የአለማችን ረጅሙ የዱባዩ ''ቡርጂ ከሊፍ'' ህንፃ ነው።

✅ ስጋ በሎች ነፍስ ገዳይ አትክልት በምድር ላይ እንዳሉ ያውቃሉን? 550 የሚያክሉ ስጋ በል መኖራቸው በምርምር ታውቋል። ከነዚህ መካከል ''ሪቬነስ ፍላይ ትራፕ'' እና ''ሃንጊንግ ፒቸር ፕላንትስ'' የሚባሉት በሰሜን አሜሪካ የካሮላይ ግዛትና ረግረጋማ ቦታዎች እንዲሁም በደቡባዊ ምስራቅ ኤስያ አከባቢዎች ይገኛሉ።

✅ የእስስት ምላስ የመዘርጋት ፍጥነት ከጀት አውሮፕላን ፍጥነት ይበልጣል።

✅ የአለማችን ታላቁ ሳይንቲስት አልበርት አንስታይን መኪና መንዳት አይችልም። በተፈጥሮው ካልሲ እድርጎ አያውቅም።

✅ ለአካለ መጠን የደረሰ ሰው በሴኮንድ 100 እንዲሁም በቀን 86,000,000 የስፐርም ሴሌችን ያመነጫል።

image
Like
Comment
Share
ቤተ መጻሕፍት profile picture
ቤተ መጻሕፍት
6 months ago

አንድ ወጣት የዩንቨርሲቲ ተማሪ ከፕሮፈረሰሩ አስማሪው ጋርመናፈሻው ላይ ቁጭ ብለው ያወራሉ አስተማሪው ከተማሪዎች ሁሉ ይህን ተማሪ
በጣም ስለሚወደው እንደ ጓደኛው አድርጎ ነው ሚያየው፡፡

ፊት ለፊታቸው ጫማውን አውልቆ የመናፈሻውን ጵዶችና ሳሮችን
የሚያስተካክል ሰራተኛ አለ፤ተማሪው የጵዳት ሰራተኛውን እያየ ለአስተማሪው “ቲቸር ዛሬ አንተም እኔም ደብሮናል፤ ለምን ያኛውን ሰውዬ ትሪክ አንሰራውም? ያወለቀውን ጫማ ደበቅ እናርግበትና ጫማዎቹን ሲያጣቸው እንዴት እንደሚበረግግ እኛም እዛጋ ደበቅ ብለን እንመልከተው” ይለዋል፡፡

አስተማሪውም“ወጣቱ ጓዴ ምንም እንኳ ቢደብረን ድሃዎችን
እያሰቃየን እኛመደሰት የለብንም፡፡ ባይሆን እኛ ገንዘብ አለን በገንዘባችን የበለጠ ደስታን ማግኘት እንችላለን፤ ሂድና ቀስ ብለህ ሰውዬው ሳያይህ ባወለቀው ጫማዎች ላይ ገንዘብ ከተህበት ና፤ ከዛምተደብቀንየሚሆነውን እናያለን” አለው፡፡

ተማሪው አስተማሪውእንዳለውቀስ ብሎ የሰውዬው ጫማላይ በርካታ ገንዘብ ከቶበት መጣና ከአስተማሪው ጋርደበቅ ብለው የሰውዬውን ሁኔታ መከታተልጀመሩ ሰውዬው ፅዳቱን ጨርሶ ኮቱን ለበሰና ጫማውን ለማድረግሲታገል ይቆረቁረውና ጎንበስ ብሎ ጫማውን
ሲያራግፈውብሮችን ያገኛል ሰውዬው ደነገጠ!! ዙሪያውን ቢያይ ማንም የለም፤ ደግሞ ደጋግሞ ቀኝና ግራ ሲመለከት ማንም ሰው የለም፡፡

ሰውዬው በአግራሞት አንገቱን እየነቀነቀ ገንዘቡንኪሱ ውስጥ ከከተተው በሗላ ሁለተኛ እግሩጫማውን ለማድረግ ሲያነሳ
በተመሳሳይ ገንዘብ ያገኛል ሰውዬው አላመነም!! በጉልበቱ ተንበረከከ አንገቱንም ወደ ሰማይ ቀና አደርጎ ጮክብሎ “ጌታዬ የሚስቴን መታመም አውቀህ ነው አይደል፤ካንተ ሌላ ማንም እንደማይረዳት አውቀህ ነው አይደል!! የልጆቼ ዳቦማጣታቸውን አይተህ ነው አይደል!!
ምስጋና ይግባህ ጌታዬ” አለ፡፡

ተማሪው የሰውዬውን ሁኔታ ሲመለከት ልቡን ነካው አይኑ እንቧ አቀረረች አስተማሪውም “ቅድም ካሰብከው ትሪክይልቅ አሁን የተሻለ ደስታ እንዳገኘህ አልጠራጠርም” አለው።

ተማሪው እንባውን እየጠረገ “ፕሮፌሰር እስከዛሬዐካስተማሩኝ ሁሉ እንደዚህ ያለ ትምህርት አስተምረውኝ አያውቁም፤ በህይወቴ የማረሳውን ትምህርት ነው ያስተማሩኝ፤ እውነትም ከመቀበል መስጠት የተሻለ ነው” በማለት መለሰላቸው፡፡

"ደግ ደጉን እናስብ መልካምነት መልሶ ይከፍላልና።

image
Like
Comment
Share
Load more posts
    Detail
  • From Ethiopia

  • Male
    More info
    My photos 
    0
    Following 
    342
  • Ethiotutor
    Spainiesth
    Chad Kerne
    denisepeel
    niriam
    inceroxzen
    Myra Ether
    Scorchiest
    Lemma Mege
    Followers 
    210
  • Tik Tok Fu
    jamieecox
    Jackson He
    julius aka
    micchmurph
    Lyte Advan
    Prime Natu
    oteasbarge
    andredeenn
    Likes 
    48
  • Xibaara Sh
    Ethiopian
    ጠቅላላ እውቀት
    Ethiopian
    Ethiopian
    Oromia Cle
    The Bible
    Bible
    ጎጂ ልማድ
    Groups 
    28
  • We are Afr
    ፈገግታ ግሩፕ
    ተነቃቅተናል
    የሳቅ መንደር
    Africa
    ስለኮሮና እናውራ
    አብረን ኖረን አ
    ቃና ውስጤ ነው
    የፍቅር ቃል

© 2021 ExpressAfrica

Language
  • English
  • Amharic
  • Afaan oromoo

  •   FAQs 
  • See COVID-19 Update
  • More
    • Privacy
    • Community Standards
    • About
    • News & Blogs
    • Pay
    • Money policy
    • Africa
    • FAQs
    • COVID-19 (Coronavirus) Updates

Unfriend

Are you sure you want to unfriend?

Report this User

Important!

Are you sure that you want to remove this member from your family?

You have poked Bookstore

New member was successfully added to your family list!

Crop your avatar

avatar


Language
  • English
  • Amharic
  • Afaan oromoo
  • Home
  • About
  • Privacy
  • Community Standards
  • Help
  • News & Blogs
  • More
    • Pay
    • Money policy
    • Africa
    • FAQs
    • COVID-19 (Coronavirus) Updates

© 2021 ExpressAfrica

Comment reported successfully.

Post was successfully added to your timeline!

You have reached your limit of friends!

File size error: The file exceeds allowed the limit (244 MB) and can not be uploaded.

Unable to upload a file: This file type is not supported.

We have detected some adult content on the image you uploaded, therefore we have declined your upload process.

Share post on a group

Share to a page

Share to user

Your post was submitted, we will review your content soon.

To upload images, videos, and audio files, you have to upgrade to premium member. Go Premium Service

Edit Offer

0%

Sell new product

Seller Contact
0%