አንድ የፐርሺያ ንጉስ ፤ በሶስት ሰዎች ላይ የሞት ፍርድ ፈርዶባቸው የስቅላት ስነስርአቱ ከመፈፀሙ በፊት ለመጨረሻ ጊዜ የሚሉት ነገር ካለ እንዲናገሩ ለእያንዳንዳቸው እድል ሰጣቸው ። የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ሰዎች ተስፋ በቆረጠ ስሜት ውስጥ ሆነው እያለቀሱ ቤተሰቦቻቸውን ተሰናበቱ ።

የሶስተኛው ሰውዬ ተራ ሲደርስ ግን ሰውዬው ንጉሱን አንድ ጥያቄ መጠየቅ እንደሚፈልግ ተናገረ ። ንጉሱም "በል ተናገር" ብለው ፈቀዱለት ። ሰውዬው ንጉሱን "የስምንት ወር እድል ከሰጡኝ የሚወዱትን ፈረሶን አሰልጥኜ ክንፍ አብቅሎ እንዲበር ማድረግ እችላለው!" ሲል ለንጉሱ ተናገሩ ። ንጉሱም ደስ እያላቸው" ስምንት ወር ይበዛል ባይሆን ሁለት ወር ልሰጥህ እችላለው "።

ነገር ግን ፈረሴ በሁለት ወር ውስጥ ክንፍ አብቅሎ መብረር ካልቻለ ተሰቃይተህ እንድትገደል አደርግሃለው! "አሉት ። ሰውየው በዚህ ተስማማ ። ይህን የሰሙት አብረው ስቅላት የተፈረደባቸው ሰዎች " አንተ ሰውዬ መቼስ ፈረስ ክንፍ አውጥቶ እንደማይበር ታውቃለህ ። ታዲያ ይሄን እያወክ ተሰቃይተህ ለመሞት እንዴት ትስማማለህ...ቆይ ምን አስበህ ነው ?" ብለው ጮሁበት ። ሰውየውም እንዲ ሲል መለሰላቸው "አስቡት እስኪ...በዚህ ሁለት ወር ውስጥ
አራት አማራጮች አሉኝ፦ አንደኛ ማንም ሳይገለኝ በተፈጥሮ ሞት ልሞት እችላለው ። ሁለተኛ ፈረሱ እራሱ ሊሞት ይችላል ። ሶስተኛ ንጉሱም ሊሞት ይችላል ። አራተኛው ደግሞ ማን ያውቃል ፈረሱ እራሱ ክንፍ አውጥቶ መብረር ቢችልስ ? አላቸው ።

ተስፋ ባለመቁረጡ አንገቱ ላይ የጠለቀችውን ገመድ በጥሶ ጥሏታል። አበቃለት በተባለበት ሰዓት እሱ ግን በተስፋ አዲስ ፀሐይ እንደምትወጣ ያምን ስለነበር ይህወቱን ለማትረፍ ችሏል ። አስቸጋሪ በተባለ ሁኔታ ውስጥ ብንሆን እንኳ እይታችን የተስተካከለና ወደ ኋላ ከሚጎትተን አሉታዊ ሀሳቦች ከራቅን አማራጭ መንገድ ሁሌም በየትም ቦታ አለ ። የጥዋት ፀሐይን ለመሞቅ ድቅድቁን ጨለማ ማለፍ ግድ እንደሆነ ሁሉ ፤ አብቅቶለታል የተባለው ነገር ለአዲስ የህይወት ጅማሮ መማሪያና መንደርደሪያ ሊሆን እንደሚችል ማመን አለብን ብዬ አስባለው።

"አልማዝ ሳይሞረድ እንደማያንፀባርቅ ሁሉ ስብዕናም ያለመከራ ቦግ አይልም" እንደሚል ፈላስፋው ወርቅ በእሳት በመፈተኑ ነው ተፈላጊና ውድ የሆነው ። የተስተካከለ አስተሳሰብና እይታ ያለው ሰው ከችግር
ውስጥ አማራጭ መንገድ እንዳለ ፣ የመፍትሄ ሀሳብን ያፈልቃል እንጂ
በደረሰበት ችግር ተስፋ ቆርጦ እጅ አይሰጥም ። ተስፋ መቁረጥ ያለብን በተስፋ መቁረጥ ላይ እንጂ በህይወታችን ላይ ሊሆን አይገባም የነገዋ ጀምበር የነገዋ ፀሀይ ምን ይዛ እንደምትመጣ አይታወቅምና።

image
About

ከዓለም መጻህፍት የምናገኘውን አንካፍላለን