ዓውደ መንፈስ Cover Image
ዓውደ መንፈስ Profile Picture
ዓውደ መንፈስ
@awudemenfes
100 people like this
+251913961553
ዓውደ መንፈስ is feeling Blessed
3 months ago - Youtube

#በምን_በምን_እንመስላት (ከግጥሙ ጋር) - በዘማሪት ወርቅነሽ ተፈራ (የዱሮ መዝሙር)
https://youtu.be/8AUtrxXhC0Y?list=RD8AUtrxXhC0Y

#የቅዱሳን_ሥዕላት_ክብር

ቅዱሳን ሥዕላት የከበሩ ናቸው፡፡ ጠቀሜታቸው ከፍተኛ በመሆኑ በቤተክርስቲያን ይሣላሉ፡፡ ይሁን እንጅ ምዕመናንም ቅዱሳን ሥዕላትን ለተለያዩ አገልግሎቶች ስለሚጠቀሙባቸው እያሣሉ በቤታቸው ይገለገሉባቸዋል፡፡ እዚህ ላይ ግን ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል፡፡ ቅዱሳን ሥዕላት ለግድግዳ ጌጥነት የምንጠቀምባቸው አይደሉም፡፡ በክብር በተለየ ቦታ በመጋረጃ ተጋርደው ለጸሎት በምንጠቀምበት ልዩ ቦታ ላይ ሊደረጉ ይገባል፡፡ በመሆኑም አስፈላጊ ባልሆነ መንገድ መጠቀም ጉዳት እንጅ ጥቅም የለውም፡፡ አሁን በብዛት የምናስተውለው ለቅዱሳን ሥዕላቱ የምንሰጠው ክብር በጣም የቀነሰ መሆኑን ነው፡፡ ስዕላትን ለጌጥ፣ ለማስታወቂያ፣ እነዲሁም በኮፊያ እና በተለያዩ ልብሶች ላይ መጠቀም ተገቢ አይደለም፡፡

#ለጌጥነት_አለመጠቀም፡-
ብርጭቆ ላይ ለቤት ማስጌጫነት ለመኝታ ቤት ማስጌጫነት ለቤትና ለመኪና ቁልፍ መያዣነት መጠቀም፣ ለመኪና መስኮቶች ጌጥነት ተገቢ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ለምሳሌ መኪና ውስጥ ስትመለከቱ ሲጋራ ይጨስባቸዋል ይቀደዳሉ ጫት ይቃምባቸዋል ወዘተ ስለዚህ የተከለከለ ነው፡፡

#ልብስ_ላይ_አለማድረግ፡-
ኮፊያ ከነቴራ ላይ መሣል ተገቢ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ልብሱ ይቆሽሻል ያ ማለት ሥዕሉንም እናበላሸዋለን ማለት ነው፡፡ ሲቆሽሽ ታሽቶ ይታጠባል በዚህም የተነሣ ሥዕሉ ይላላጣል፡፡ ስለዚህ በተለይ ለክብረ በዓላት ቅዱሳን ሥዕላትን የምናሳትም ወገኖች ጥንቃቄ ብናደርግ ጥሩ ነው፡ ለበረከት ስንል ለመቅሰፍት እንዳይሆንብን፡፡

#ሥዕላትን_ለማስታወቂያ_አለመጠቀም፡-
አንዳንድ ነጋዴዎችና ድርጅቶች በሚያመርቱት ምርት ላይ ቅዱሳን ሥዕላትን ይጠቀማሉ፡፡ ለምሳሌ ቅዱስ ጊዮርጊስን በቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ላይ እናገኘዋለን፡፡ ይህ ፈጽሞ ስህተት ነው፡፡ ሰው ይሰክራል፣ ሥዕሉን ከጠርሙሱ ልጦ ይጥለዋል፣ ሥዕሉ ተገቢ ባልሆነ ቦታ ይወድቃል፡ ሌላው ለመዝሙር ለጉባኤ እና ለመፃህፍት ፖስተር መጠቀም ተገቢ አይደለም መክንያቱም በየመንገዱ ስለመለጠፉ ስለዚህ እንደዚህ አይነት ለቅዱሳን ሥዕላት ክብርን የሚቀንሱ ነገሮችን ከመጠቀም ልንታቀብ ተገቢ ነው፡፡

(አቤል ተፈራ በላይ)

About

የቀደሙ የዋኖቻችን፣ የአባቶቻችን ቃል።