
የሀገር ባለውለታዎች
ከጀርባ ገጽ የተወሰደ ....
በቀዳማይቷ ኢትዮጵያ ፣ ሥነ መንግሥትና አስተዳደርን ፣ ፍትሕና ፍርድን ፣ አምልኮተ እግዚአብሔርና ሥርዐቱን ፣ ማኅበራዊ ሕይወትንና የሰው ልጅን ሰላማዊ መስተጋብር፣ ሥልጣኔን፣ ሥነ-ምግባርና ዕውቀትን ለመቅሰም ከባሕር ማዶ በባዕዳን እንጎበኝ ነበር። የሚያስደምም ማንነታችን የመነጨው ከባህላችን፣ ከእምነታችንና ከቅዱሳት መጻሕፍት ነበር፡፡ በተቀደሰ ኑሮ፣ በምግባርና በጀግንነት፣ በለጋሥነትና በፍትሐዊነት ያጌጠ ነበር። ዛሬ ላይ ተቃራኒው ሆነብን። በአንድነትና ፍቅር ከጠላት ተከላክለው ያስረከቡንን ሀገር አፍርሰን የባዕዳን ተመጽዋች ሆንን። አሳብ፣ ፖለቲካና ሥነ-አስተዳደር እንዋሳለን፤ ያልኖርነውን ታሪክ በምናብ ስበን እውነትን ጥለን እንዋሻለን፡፡ ራሳቸውን ችለው ራሱን የሚችል ትውልድ እንዲኖር ሕይወታቸውን የገበሩልንን የዐርበኞቻችንን ድካም ከንቱ አደረግን፤ ሕልማቸውን አጨልመን፡፡ እነርሱ ድል የነሱት የኢትዮጵያ ጠላት በትምህርት ስም የጫነብንን የማይጨበጥ ቅዠት እንኖራለን። አርበኞቹን የገደሉት ባዕዳን ሳይሆኑ፣ የተሸናፊ ጠላት መንፈስ ማኅደር በመሆን እርስ በእርሳችን ለውክልና ጦርነት የተሰለፍን እኛ ከአንዴም ሁለቴ ገደልናቸው።
ሀገራችንን ከሚያኮራ ታሪክ ፣ ከሚያስመሰግን እምነትና ባህል፣ ከሚያስከብር ጀግንነት ጋር ያስረከቡንን አባት እቶቻችንን በበዓላት ከመዘከር አልፈን በሕይወታችን ልንገልጻቸው ይገባል፡፡ የቀዳማዊቷ ኢትዮጵያ የታላቅነት ምሥጢር ተዋሕዶ ያፈለቁት ሀገር በቀል ዕውቀት የሀገራዊ መሠረት ጀግኖችን ፈጠረለን። ግና በዐዲስቷ ኢትዮጵያ ያሉት ልሒቅ ለዚህ የታላቅነት መሠረት ጠላት ሆነው ተነሡ፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ኋላቀር፣ ወራሪ፣ የጨቋኞች መሪ አሏት፣ አሳደዷት፣ ልጆቿን ስደተኛና ሙት አደረጓት። ዛሬ ላይ እንደዐድዋ ያሉ ዓለም አቀፍ ድልና ሌሎች በአንድነታችን ያገኘናቸውን መልካም ድሎች፣ የፈጠርና....