በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥር 600 ደረሰ!
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 21,326 የላብራቶሪ ምርመራ 1,336 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ28 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 370 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 34,058 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 600 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 13,308 ደርሷል።
