በትላንትና እለት በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ጋምቤል ወረዳ፣ ቦኔ ቀበሌ ውስጥ የተፈፀመው ጥቃት የበርካቶችን ህይወት ቀጠፈ።
የ "ሰዴቃ" ቲክቫህ አባላት ትላንት ምሽት 2:00 ላይ በርካታ ንፁሃን በሚያሳዝን ሁኔታ መገደላቸውን አሳውቀዋል።
ታጣቂዎቹ በከባድ እና አውቶማቲክ መሳሪያ ጭምር ነው ግድያ የፈፀሙት።
እስካሁን 28 ሰው የተቀበረ ሲሆን ወደ ጤና ተቋም ወደ 15 የሚደርስ ሰው ተወስዷል፥ የመትረፋቸው ነገር አጠራጣሪ ነው ብለውናል።
በርካቶች ጥቃቱን ሸሽተው ጫካ ውስጥ ተሸሽገው ነው ያደሩት።
የሚሰማን አካል ካለ ከአካባቢው መውጣት ነው የምንፈልገው ብለዋል።
በተጨማሪ አንድ የዛው አካባቢ ተወላጅ የሆነ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል በትላንቱ ጥቃት ሁሉም ጓደኞቹ እንደሞቱበት ተናግሯል።
አካባቢው ላይ እንዲህ አይነት ድርጊት እንደሚፈፀም ይታወቅ ነበር ያሉት አባላቶቻችን ከዚህ በፊት "ታጣቂዎች" አካባቢውን ለ7 ቀን ያህል ይዘውት ነበር ፥ ነገር ግን መንግስት ይሄን እያወቀ ምንም አይነት ጥበቃ ሊያደርግ አልቻለም ብለዋል።
ጉዳዩ ውስብስብ ያለ ሆኖብናል ሲሉ ገልፀዋል።
ከሰዎች ግድያ በተጨማሪ ቤቶችም ስለመቃጠላቸው አባላቶቻችን ገልፀዋል።
ትላንት ጥቃቱ ሲፈፀም ምንም አይነት የፀጥታ ኃይል ያልደረሰ ሲሆን ዛሬ ከነጋ ነው ቦታው ላይ የደረሰው። አሁን ላይ የወረዳው ሚሊሻ፣ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ እና የአካባቢው ፖሊስ ቦታው ላይ ይገኛል።
የክልሉ መንግስት በንጹሃን ዜጎች ላይ ጥቃት መፈፀሙን እና ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ዜጎች መገደላቸውን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አረጋግጧል።
ጥቃቱ በፈጸሙ የተወሰኑ ኃይሎች ላይ እርምጃ ወስጃለሁ ብሏል።
በየቀኑ በሀገራችን የሚንሰማው አድስ ነገር ሊያሳስበን ይገባል። በእርግጥ ሀገራችን ጦሪነት ላይ ናት። ያውም ደግሞ ሁለት ልጆቿ እየተዋጉ ነው። በዝህን ሰዓት ደግሞ full range ጦርነት ነው እየተደረገ ያለው። ይሄ ማለት ሁላችንም የጦሪነቱ ሰለባ ነን ማለት ነው። መቼ እንደምንመታ አናውቅም። በጦሪነት እርግጠኛ የምትሆነው ስታሸንፍ ብቻ ነው። በሚዲያ ብዛት፣ በውሸት ብዛት፣ በመሳሪያ ብዛት ጦርነት ማሸነፍ አትችልም። ጦሪነት በcause ነው የምታሸንፈው። selflessly ራስህን፣ ህዝብህን እና idologyን ለመጠበቅ ስትዋጋ ታሸንፋለህ።
ብዙ ማለት ይቻላል። ግን ከጦርነት ትርፍ የለም። ጦርነት አውዳሚ ነው። ከተቻለ ወደ ውይይት መመለስ ተገቢ ይመስለኛል። እኔ ሁለቱንም አካላት አልደግፍም። እኔ ሰላምን፣ civilityንና አንድነትን ነው የሚፈልገው። ከስሜታችን ህዝብ ይቅደም።
አመሰግናለሁ።
ቀኑ ማለፉ አይቀርም። ጦርነት promote ያደረጉ ስያለቅሱ እኛ atleast የህልና ሰላም የምናገኝበት ግዜ ሩቅ አይመስለኝም።
ዶር ሆይ ከጦርነቱ ፀሎቱ ሳይሻል ስለማይቀር ወደ ፈጣሪ ተመለስ።