በህክምና ትምህርት ቤት የተለመደ የሆነውን የቃል ፈተና ለመፈተን ተማሪው ገብቶ ተቀምጧል። ፈታኙ ሲኒየር ሐኪም ተማሪውን መጠየቅ ጀመረ…
.
ሲኒየር: "አውቶቢስ ውስጥ ተሳፍረህ እየሄድክ ሰው በመብዛቱ ሙቀቱ ቢያስቸግርህ ምን ታደርጋለህ?"
.
ተማሪ: "መስኮቱን እከፍታለሁ።"
.
ሲኒየር: "በጣም ጥሩ፤ … እንበልና አውቶብሱ 80 ኪሎሜትር በሠአት እየተጓዘ ከሆነ፣ ከመስኮቱ ሁለት ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ከአንተ አጠገብ ያለ ተሳፋሪ በመደበኛ አተነፋፈስ ወደሳንባው በደቂቃ ምን ያህል ካርቦንዳይኦክሳይድ ይደርሰዋል?
.
ተማሪ: (ቁልጭ ቁልጭ እያለ ረጅም ዝምታ)
.
ሲኒየር: "እሺ ወድቀሃል በቃ ፣ ቀጣይ ተፈታኝ ይግባ"
.
[*ተማሪው በጣም እያዘነ ወጥቶ ለቀጣዩ ተፈታኝ ያጋጠመውን ነገረው። ሁለተኛው ተማሪም ጥያቄውን እያብላላ ለፈተና እንደገባ ሲኒየሩ ያንኑ ጥያቄ ጠየቀው።*]
.
ሲኒየር: "አውቶቢስ ውስጥ ተሳፍረህ እየሄድክ ሰው በመብዛቱ ሙቀቱ ቢያስቸግርህ ምን ታደርጋለህ?"
.
ተማሪ 2: ጃኬቴን አወልቃለሁ።
.
ሲኒየር: ሙቀቱ ይበልጥ እየጨመረ ቢሄድስ?
.
ተማሪ 2: ሸሚዜንም አወልቃለሁ።
.
ሲኒየር: (በአግራሞት እየተመለከተው) "እሺ ሙቀቱ ከመጠን በላይ ሁኖ ባሱ እንደ እሳት ማቃጠል ቢጀምርስ?
.
ተማሪ 2: "ዶክተር በእውነት ቆዳዬ ቢላጥ እንኳን መስኮቱን አልከፍትም።"
.
ዶ/ር ሰኢድ ያሲን ፣ የአጥንት ህክምና ስፔሻሊስት fb Hakim