#ተጨማሪ
" የስራ ሰዓት ከጠዋቱ 12 ሰአት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ብቻ ነው " - የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ
ተቋርጦ የነበረው የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት ከነገ ጀምሮ ባጃጆቹ በተመደቡላቸው መስመሮች ብቻ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።
በመግለጫው ምን ተባለ ?
- ከአገልግሎቱ ጋር በተያያዘ ለተፈጠሩ ችግሮች መንስኤ ናቸው የተባሉት ፦
• ህግን አክብሮ አገልግሎት አለመስጠት፣
• በአብዛኛው አሽከርካሪ ዘንድ ደረጃውን የሚመጥን መንጃ ፍቃድ አለመያዝ
• የታሪፍ ስርዓት አለመኖር ዋንኞቹ ናቸው።
- አሁን በተዘጋጀ መመሪያ መሰረት ቢሮው በለያቸው የስምሪት መስመሮች አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጿል።
- 138 ጊዜአዊ ታፔላዎችን ከዋናው መስመር ውጪ ተዘጋጅተዋል።
- የትራፊክ ምልክቶች ተከላ ማከናወን እና ማህበራትን ማደራጀት ዋንኛ ስራ ነበር። በ8 ክ/ከተሞች 123 ማህበራትን የማደራጀት ስራ የተሰራ ሲሆን አገልግሎቱም በኮድ 1 ታርጋ ብቻ ይሰጣል።
- የተሳፋሪ መጠን አሽከርካሪውን ጨምሮ 4 ሰው ብቻ ሴሆን የስራ ሰዓት ከጠዋቱ 12 ሰአት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ብቻ ነው። ህጉን ተላልፈው የተገኙ አሽከርካሪዎች በየደረጃው ቅጣት ይጣልባቸዋል።
- በከተማው መደበኛ ትራንስፖርት በማይገኝበት ከ0 ነጥብ 9 እስከ 2 ነጥብ 45 ኪሎ ሜትር ርቀት ብቻ በ5 ብር ታሪፍ አገልግሎት እንዲሰጡ ተወስኗል።
- የባጃጅ ተሽከርካሪዎች በየትኛውም ርቀት ከ5 ብር በላይ ማስከፈል አይችሉም።
Credit : ADDIS MEDIA NETWORK / FBC
#tikvah
