"የአፍሪካ ሀገራት የሱዳንን መንግስት ምከሩት" - ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ መንግስት በዛሬው ዕለት ምሽት ባወጣው የፕሬስ መግለጫ ኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይ በሰላማዊ መንገድ በውይይት ይፈታ ዘንድ ኢትዮጵያ ቁርጠኛ መሆኗን በድጋሚ አረጋግጧል።
ወዳጅ የሆኑትን የኢትዮጵያ እና የሱዳን ህዝቦች ወደአላስፈላጊ ጦርነት ለማስገባት በሱዳን ጦር እየተደረገ ያለው ሙከራ የሁለቱን ሀገራት እንዲሁም በአጠቃላይ የቀጠናውን ሰላም ፣ መረጋጋት እና እድገት የሚሸረሽር ከባድ ስህተት ነው ብሏል።
የኢትዮጵያ መንግስት ፥ የሱዳን ህዝብ የሀገራቸው መንግስት ለሶስተኛ ወገን ፍላጎት መጠቀሚያ እየሆነ እንዳለ እንዲያረጋግጡም ጥሪ አቅርቧል።
የአፍሪካ ሀገራት የሱዳን መንግስት የድንበሩን ጉዳይ ባለው አማራጭ በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲፈታ ምከሩት ብሏል።
ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይ ጥልቅ ግንዛቤ ላለው እንዲሁም ከፍተኛ ትዕግስት ላሳየው የኢትዮጵያ ህዝብ የኢፌዴሪ መንግስት ምስጋና አቅርቧል።
* ዛሬ ምሽት በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል የወጣውን መግለጫ ሙሉ ሀሳብ ከላይ በታይያዘው ምስል ማግኘት ትችላላችሁ።

