እንኳን ደስ አላችሁ
ለ<<አጤጤሳቢኮ>> ተመራቂዎችና ለክላስ ጓደኞቼ!
በቅድሚያ እንኳን የድካማችሁን ፍሬ ለማየት አበቃችሁ።
"የድካምህንም ፍሬ ትመገባለህ፤ መልካምም ይሆንልሃል።"መዝ128 : 2 እንዲል...
እንግዲህ ለሰው ልጅ፥ ጊዜን የማስቆም ስልጣን ስላልተሰጠው እንጂ ስልጣኑ ኖሮኝ ጊዜን አስቁሜ ከእናንተ ጋር ተማሪ ሆኜ ረጅም ጊዜ መቆየት ብችል እንዴት ደስ ባለኝ ...።
ከእናንተ ጋር ሆኖ፥ "ሺህ ዓመት እንደ አንድ ቀን ናት"። አብረን ሆነን ያሳለፍናቸው መልካም ጊዜያት፥የሚጠገቡ ባለ መሆናቸው ተጨማሪ ጊዜን የሚያስጠይቁ ናቸው።. .ግን ያው እንደምታውቁት ቀሪውን የህይወት ጊዜ መታገል ግዴታ ስለሚሆንብን አምነን እንቀበለዋለን።በእኔ በኩል ከትምህርት ቤት ከገኘሁ እውቀት ይልቅ ከእናንተ የተማርኩት በእጅጉ ያስደስተኛል። ብዙ ጠቃሚ ነገሮችን እርስ በእርስ ተምረናል።ብዙ አስቂኝ ጊዜያት አብረን አሳልፈናል። Birhanu Asefa Presentation ቀን ከምሽቱ 1:05 ክላስ አንኳኩቶ ሲገባና ተጨማሪ ማብራሪያ ሊሰጥ እጁን ሲያነሳ ፣ awraris ያልተመቸውን አስተማሪ በቁሙ ትቶት ከክፍል ሲወጣ!#ከጠ/ሚ መምጣት በፊት ነፃነቱን ያወጀው ብቸኛው ሰው !! Belete የትምህርት ዓይነቱን ፈተና ላይ ቁጭ ብሎ ሲጠይቅ፣ #muller 30 ጥያቄ በ3 ደቂቃ ውስጥ ሰርቶ ሲያስረክብ፥ #abe አስተማሪን በጥያቄ ሲያፋጥጥ፥ ለአስተማሪ ይቀየርል ጥያቄ አስተያየት ለመስጠት ከክፍል 27 እጅ ሲወጣ ፣እረ የእናንተ ነገር ደስ ሲል...ብቻ ከብዙ በጥቂቱ በቅርበት ከማቃችሁ፥የ Birhanu Asefa ፍቅር፣ የ Belete ታማኝነት የ Elizabeth Tamene ትዕግስት፣ የ awraris በራስ መተማመን፣ የ Getachew ነፃነት፣ የ Tadele hailu ዝምታ፣(ትርጉም ከሌለው ንግግር ትርጉም ያለው ዝምታ ይሻላል) አባባሉ ሳይቀር፣የ #elsabeth ጥረት፣የ #tekabe ጥንካሬ፣ የ Kal ሥርዓትና ሰው አክባሪነት፣ የAfomiya Mulugeta ታታሪነት፣ ሁሌም እንዳስገረመኝና እንዳስተማረኝ!
መቼም የተማራችሁት፥ ትልቅ ራዕይ ካላቸው ሰዎች ተርታ በመሠለፍ፥
ውስብስቡን የሰውን ልጅ ፈተና እና ውጣ ውረድ ለማቃለልና ለመቅረፍ፣ በጥቂቱም ቢሆን ለመታገል እንጂ ፣ ለእለታዊ ጥያቄአችሁ መልስ ለመስጠት ብቻ እንዳልሆነ እምነት አለኝ። እደምታደርጉም ተስፋ አደርጋለሁ።እየሰሩ መማር፣ እየተማሩ መስራት ይሉታል #ሜቴኮች
በመጨረሻም #ፕሮፌሰሩ እንዳሉት መማር ለባህርይ ለውጥ መሆን እንዳለበት ለእናንተ አልነግራችሁም።
የእውቀት ሁሉ መጨረሻ መልካም ስራ ነው። የሰዎችን ክፉ ስራና ሴራ እያዩ ወደኋላ መመለስ ሳይሆን፥ የታላላቅ ሰዎችን ምሳሌ በመከተል ወደፊት መጓዝ መማርን ሙሉ ያደርገዋል።
እንደገና፥እንኳን ደስ አላችሁ!!