የነዳጅ ዋጋ 📈
ከነገ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሬ መደረጉን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳውቋል።
በዚህ መሰረት ፦
⛽️ ቤንዚን ➡️ 47. 83 በሊትር
⛽️ ነጭ ናፍጣ ➡️ 49.02 በሊትር
⛽️ ኬሮሲን ➡️ 49.02 በሊትር
⛽️ ቀላል ጥቁር ናፍጣ ➡️ 53.10 በሊትር
⛽️ ከባድ ጥቁር ናፍጣ ➡️ 52.37 በሊትር
⛽️ የአውሮፕላን ነዳጅ ➡️ 98.83 በሊትር መሆኑን አስታውቋል፡፡
ከላይ የተገለጸው የቤንዚን ፣ የኬሮሲን እና የነጭ ዋጋ ላይ ለህዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች ወይም የታለመ ድጎማ ተጠቃሚ ተሸከርካሪዎች 15 በመቶ በመንግስት እንዲደጎሙና ቀሪውን 10 በመቶ እንዲከፍሉ በማድረግ የድጎማ መጠኑን በቴሌ ብር ተመላሽ እንዲሆንላቸው ይደረጋል ተብሏል።
የተደረገው የዋጋ ማስተካከያ የተደረገባቸው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በዝርዝር ከነገ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክልሎች በሚገኙ ማደያዎች ሁሉ ተግባራዊ ይሆናል።
ምንጭ፦ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር
All about The Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD) | #the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD)
ትግራይ ክልል ውስጥ ባሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ልጆቻቸውን ልከው የሚያስተምሩ ወላጆች ከፍተኛ የሆነ ጭንቅ ውስጥ ናቸው!
ለመሆኑ ይህ ሁሉ ሺህ ቤተሰብ በመላው ሀገር ሲጨነቅ አጭር መግለጫ ብጤ የሚሰጥ እንኳን የለም? ደግሞስ "ከትግራይ እንደምንወጣ ከሳምንታት በፊት የነገርናቸው የውጭ ተቋማት ነበሩ" ከተባለ ለተማሪዎች ደህንነት ሲባል ቢያንስ በግዜያዊነት ወደመጡበት እንዲመለሱ ለምን አልተደረገም?
በማህበራዊ ሚድያው ላይ እንደተለመደው ነገሮችን ለማወሳሰብ ሙከራዎች መደረግ ጀምረዋል። እንደዛም ሆኖ እጅግ በርካታ ቤተሰቦች አፋጣኝ መልስ ይፈልጋሉ።